በትናንትው ዕለት ረቡዕ ጥር 19 ቀን 2013 ዓ/ም የኢትዮጵያ ስራ አመራር ኢኒስቲትዩት እና የአዲስ አበባ ወጣቶችና በጎ ፍቃድ ቢሮ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ለመስራት ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡በስምምነታቸው መሠረት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት በመጪዎች አስር ዓመታት የሚመራበት ፍኖተ ካርታ በቀጣይ ሁለት ወራት ውስጥ ይጠናቀቃል የሚለው ይገኝበታል፡፡
ከዚህ በተጨማሪ በአዲስ አበባ የሚካሄዱ የበጎ አድራጎት ስራዎችን ህጋዊ ሰውነት ለማላበስ በሚል የበጎ ፍቃድ አገልግሎት አሰጣጥ መመሪያ ተዘጋጅቷል፡፡መመሪያው ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታዎች እንዳሉት የገለጹት የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶችና በጎ ፍቃድ ምክትል ቢሮ ሐላፊ አቶ ፍሰሃ ጥበቡ ናቸው፡፡
አሐዱ በዚህ የበጎ ፍቃድ አገልግሎት እስካሁን ምን ዓይነት እክሎች ስላገጠሙ ነው መመሪያው ያስፈለገው ሲል ምክትል ቢሮ ሐላፊውን ጠይቋል፡፡ሐላፊው ምንም እንኳን በዝርዝር ሊቀመጥ የሚችል ችግር ባያጋጥምም የመመሪያው መዘጋጀት አስፈላጊነት ግን አያጠያይቅም ብለዋል፡፡
*******************************************************
ቀን 20/05/2013
አሐዱ ራዲዮ 94.3