12.5 C
Ethiopia
Friday, March 29, 2024

በአማራ ህዝብ ላይ የሚደረሰው ሞትና መፈናቀል በሚገባው ልክ በመንግስትና በፖለቲካ ፓርቲዎች እውቅና አልተሰጠውም ሲል የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) ወቀሰ፡፡

ሰላማዊ መንገድን ለማመቻቸት የሚጥሩ አባላትና አመራሮች ላይ እየደረሰ ያለው ሞትና ማሳደድ ትግሌን አያስቆመውም ብሏል ፓርቲው፡፡በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች እየተፈፀሙ ባሉ ጥቃቶች የአማራ ህዝብ ላይ ሞትና መፈናቀል እየተከሰተ መሆኑን ፓርቲው ገልጻል፡፡

የአብን የፖለቲካ ጉዳዮች ሀላፊ አቶ ክርስቲያን ታደለ በአሃዱ ሬድዮ ልሳነ ምርጫ 2013 ላይ በነበራቸው ቆይታ እንደገለጹት፤ የአማራ ህዝብ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች እየደረሰበት ያለውን ሞትና መፈናቀል አስመልክቶ በመንግስትና በፖለቲካ ፓርቲዎች በኩል በቂ ሽፋን አላገኘም ብለዋል፡፡ለፍትህ መታገልና መጠየቅ የሚጀመረው በአማራ ህዝብ ላይ ስለተፈጸመው በደል በግልጽ መናገር ሲቻል ነው ሲሉም ተናግረዋል፡፡

በኦሮሚያና በቤኒሻንጉል ክልል ባሉ የአብን አባላትና አመራሮች ላይ የሚደርሰውን ግድያና ስቃይ በተመለከተ ለምርጫ ቦርድ አቤቱታ አቅርቦ ጉዳዩ በሂደት ላይ መሆኑንም የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ አስታውቋል፡፡

ማንነትን መሰረት አድርገው የሚፈጸሙ ግድያዎችና መፈናቀሎች በርትተዋል ያለው ፓርቲው፤ ሰላማዊ መንገድን ለማመቻቸት የሚጥሩ አባላትና አመራሮች ላይ እየደረሰ ያለው ሞትና ማሳደድ የፓርቲውን ትግልና ሂደት አያስቆመውም ብሏል፡፡

ሀገርን ወደፊት ለማራመድ የሚያስችል የፖሊሲ አማራጭ ማቅረብ የሚቻለው ቅድሚያ ህዝቡ በሰላም ሲቆይ ነው ሲሉ አቶ ክርስቲያን ገልጸዋል፡፡ቀጣዩ ምርጫ በዜጎች ህልውና ላይ የተመሰረተ እንደመሆኑ፤ ከምርጫ ቦርድ ባለፈ ሁሉም ትኩረት አድርጎ ሊሰራበት ይገባል ተብሏል፡፡

ቀን 04/08/2013

አሐዱ ራድዮ 94.3

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

LIVE OFFLINE
Loading...