15.6 C
Ethiopia
Friday, March 29, 2024

በአፍሪካ የኮሮና ቫይረስ ክትባቶች የሚመረቱባቸው ሃገራት በቅርቡ እንደሚለዩ የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም ተናገሩ፡፡

ዶክተር ቴዎድሮስ ሃገራቱን ከመለየት ባሻገር ክትባቶቹን እስከተያዘው የፈረንጆቹ ዓመት  መጨረሻ ለማምረት የተቃረቡ አንዳንድ ሃገራት እንዳሉ የተናገሩ ሲሆን ሆኖም የትኞቹ ሃገራት እንደሆኑ በግልጽ አላስቀመጡም፡፡ዶክተር ቴዎድሮስ ሞደርና እና ፋይዘርን ጨምሮ ሌሎችም የኮሮና ክትባት አምራች ተቋማት የእውቀትና ምርምር ስራዎቻቸውን ለአፍሪካ ሃገራት እንዲያጋሩ እና ክትባቶቹ እንዲመረቱ ጠይቀዋል፡፡

በሃገራት መካከል ባለው የአቅም ልዩነት ምክንያት የሚፈጠሩ ኢ-ፍትሐዊ የተደራሽነት ችግሮች እንዲቆሙ ሲጠይቁ መሰንበታቸው የሚታወስ ነው፡፡በተለይም እንደ ኮሮና ዓይነት መላ የዓለም ህዝብን አደጋ ላይ የሚጥሉ ወረርሽኞች ሲያጋጥሙ ወረርሽኞቹን ለማስቆም በሚያስችሉ የፈጠራና የምርምር ስራዎች ላይ የባለቤትነት መብቶች ክልከላ እንዳይኖር እየተጠየቀ ይገኛል፡፡

ያደጉ ሃገራት በክትባቶቹ ላይ የያዙትን የባለቤትነት እና የአቅርቦት የበላይነት አቁመው የወረርሽኙ ክትባቶች አፍሪካ እና እስያን ጨምሮ በተለያዩ የደቡብ አሜሪካ ሃገራት ተመርተው በፍትሐዊነት እንዲሰራጩ ከፍተኛ ግፊት በመደረግም ላይ ነው ብለዋል ዶክተር ቴድሮስ፡፡

ዘገባው፡- የሬውተርስ ነው

ቀን 03/10/2013

አሐዱ ራድዮ 94.3

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

LIVE OFFLINE
Loading...