14.6 C
Ethiopia
Friday, March 29, 2024

በኢራቅ፣ ሶሪያና አፍጋንስታን የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ከምንጊዜውም  በላይ መክፋቱን  የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቋል፡፡

የመንግስታቱ ድርጅት በሰጠው ማብራሪያ በኢራቅ፣ በሶሪያና በአፍጋንስታን ለወረርሽኙ መስፋፋት ትልቁ ምክንያት የአይ ኤስ እና የአልቃይዳ አሸባሪዎች መስፋፋትና መጠናከር ነው ሲል ማብራሪያ ሰጥቷል፡፡የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አዲስ ባወጣው የጥናት ግኝት በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ የተነሳ የተጣለው የእንቅስቃሴ ገደብ በሶስቱም ሐገራት የዳኤሽና የአልቃይዳ ቡድኖች እንደፈለጉ እንዲንቀሳቀሱና ያሻቸውን ጥቃት እንዲፈፅሙ አድርጓቸዋል ሲል ያሳያል፡፡

የመንግስታቱ ድርጅት ባወጣው መረጃ በተለይም አሸባሪዎቹ ቡድኖች ከሰሃራ በታች ባሉት የአፍሪካ ሐገራት ያሉት መንግስታት በወረርሽኙ ክስተት የተነሳ ሃይላቸው መዳከሙንና እጅ እንዳጠራቸው ያስረዳል፡፡ባለፈው የአውሮፓውያኑ 2020 ሰኔ ወር ዴይሊ ሜይል በስዊድን የማልሞ ዩንቨርስቲውን ረዳት ፕሮፌስር ሚካኤል ክሮናን ጠቅሶ ባሰራጨው ዘገበው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝና የማህበራዊ መገናኛ ብዙሃን እንዳ አሸን መፍላት ለአሸባሪ ኃይሎች የዓለምን በርካታ አካባቢዎች ምቹ አድርጎላቸዋል ማለታቸውን ያሳያል፡፡የአይ ኤስ አፈቀላጤ አቡሃምዛ አልቁር ኤይሺ ባለፈው ጥቅምት ወር የአይ ኤስ  ጦሮች ኃይላቸውን እንዲያጠናክሩና እንዲዘጋጁ ትዕዛዝ መስጠታቸውን ያስታወሰው አህሉል ባያት የዜና ምንጭ ነው፡፡

ቀን 01/06/2013

አሐዱ ራዲዮ 94.3

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

LIVE OFFLINE
Loading...