15.2 C
Ethiopia
Thursday, March 28, 2024

በኢትዮጰያ ለኬሚካል ርጭት የሚያበቃ የአንበጣ መንጋ የለም ሲል የግብርና ሚኒቴር ገለጸ፡፡

በሀገሪቱ በተለያዩ አከባቢዎች የተከሰተውን የአንበጣ መንጋ ለመከላከል የግብርና ሚኒስቴር ሰፊ ስራ እየሰራ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡አሐዱም በተለያዩ አከባቢዎች የተከሰተውን የአንበጣ መንጋ ከመከላከል አንጻር ምን እየተሰራ ነው መንጋው ያለበት ሁኔታስ ምን ይመስላ ሲል የግብርና ሚኒስቴርን ጠይቋል፡፡

በግብርና ሚኒስቴር የዕጽዋት ጥበቃ ዳሬክተር አቶ በላይነህ ንጉሴ ለአሐዱ እንደገለጹት በኢትዮጵያ በርካታ የክልል ቦታዎች የአንበጣ መንጋ ተከስቶ የነበረ ቢሆንም በዚህ አንድ ሳምንት ውስጥ ከመንጋው መስፋፋት ጋር ተያይዞ ሪፖርቶች አለመኖራቸውን አቶ በላይነህ ገልጸዋል፡፡

በተሰራው ሰፊ ስራ ለኬሚካል ርጭት የሚያበቃ መንጋ የለም ማለት ግን የተበታተኑ የአንበጣ መንጋዎች የሉም ማለት አይደለም ብለዋል፡፡የዝናብ ወቅት አለመሆኑ ለመንጋው መጥፋት አስተዋጽኦ አድርጓል ያሉት ባለሙያው አሁን ላይ አስጊ የሚባል ደረጃ አለመኖሩን ተናግረው በቀጣይ ወራት የሚኖረው የዝናብ መጠን ከጨመረ ሊያሰጋ ይችላል ብለዋል፡፡

የዓለም ምግብ እና እርሻ ድርጅት (ፋኦ) ባወጣው መግለጫ ኢትዮጵያና ኬንያን ጨምሮ በቀጠናው የዝናብ አለመኖር ለበረሃ አንበጣው መቀነስ ምክንያት መሆኑን ገልጿል፡፡

ቀን 18/07/2013

አሐዱ ራዲዮ 94.3

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

LIVE OFFLINE
Loading...