18.3 C
Ethiopia
Thursday, March 28, 2024

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ከባድ የርሃብ አደጋ እያጋጠመን ነው ሲል ገለጸ፡፡

በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ካለው የህዝብ ቁጥር አንድ ሶስተኛው የሚሆነው ለከፋ ርሃብ መጋለጣቸውን እና አስቸኳይ እርዳታ እንደሚያስፈልግ የአለም የምግብ ፕሮግራም እና የአለም የምግብ እና እርሻ ድርጅት ገልጸው፣ በአሁኑ ወቅት 27 ሚሊዮን በላይ የኮንጎ ዜጎች አስቸኳይ የምግብ አቅርቦት ያስፈልጋቸዋል ብለዋል፡፡

ሁለቱ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ኤጀንሲዎች ያለው ሁኔታ አሰከፊ ነው ያሉ ሲሆን በተለይ ግጭት በተከሰተባቸው ማእከላዊ የካሳይ አወራጃዎች የችግሮቹ አስከፊነት ተባብሷል ማለታቸው ተሰምቷል፡፡

በአካባቢው የኮቪድ-19 ወረርሽኝ እና የምጣኔ ሀብት ማሽቆልቆል መኖሩ ችግሩን አስከፊ አድርጎታል ሲል የዘገበው ቢቢሲ ነው፡፡

ቀን 30/07/2013

አሐዱ ራድዮ 94.3

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

LIVE OFFLINE
Loading...