12.5 C
Ethiopia
Thursday, March 28, 2024

ከውጪ ሀገር የተገኘው የ4 ነጥብ 5 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የድጋፍ ገንዘብ  የሰራተኞችን  ማህበራዊ  ችግሮች  እንደሚቀንስ  የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ኮቪድ-19 ኢትዮጵያ ውስጥ ከተከሰተ ጀምሮ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እንዲሁም ፖለቲካዊ ቀውሶችን ያሳደረ ሲሆን በርካታ ቁጥር ያላቸው ዜጎችንም ከስራ ገበታቸው እንዲፈናቀሉና ደመወዛቸውን እንዲያጡ ምክንያት ሆኗል፡፡

የጀርመን መንግስት ከአለም አቀፍ የሰራተኞች ድርጅት ጋር በመተባበር በፋብሪካዎች ውስጥ የሚሰሩ ሰራተኞች በኮቪድ-19 ምክንያት የሚያጋጥማቸውን ማህበራዊ ችግር ለመቅረፍ  የ4 ነጥብ 5 ሚሊዬን የአሜሪካ ዶላር የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል፡፡የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ እንደተናገሩት በኮቮድ-19 ምክንያት በጨርቃ-ጨርቅ ኢንዲስትሪዎች ላይ ለተሰማሩ ሰራተኞች የሚያጋጥማቸውን ማህበራዊ ቀውስ ለመታደግ ስራውንም ለማስቀጠል የሚደረገው ድጋፍ ጠቃሚ ነው ብለዋል፡፡

40 ሺ ለሚሆኑ ሰራተኞች የቀጥታ ድጋፍ በገንዘብ ለሦስት ወር የደመወዝ ክፍያ እንደሚሰጣቸው ተናግረዋል፡፡በኢኮኖሚ ጉዳት ያጋጠማቸው ኢንዱስትሪዎች፣ ማህበራዊ ዋስትናን የገቡ እንዲሁም የአሰሪና ሰራተኛ አዋጁን ተግባራዊ ባደረጉ ፋብሪካዎች አማካኝነት ለሰራተኞች በቀጥታ  ክፍያው በባንክ የሚፈጸም መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የሚደረገው ድጋፍም ቀጣይነት እንዳለውም ዶክተር ኤርጎጌ ጨምረው ገልጸዋል፡፡የተደረገው ድጋፍ ሰራተኞች በስራ ገበታቸው ላይ እንዲቆዩ የሚያደርግ ሲሆን ፋብሪካዎችም በሚሰሩት ስራ  የተደረገው የገንዘብ ድጋፍ እንደሚያግዛቸው ተገልጿል፡፡

ቀን 28/05/2013

አሐዱ ራዲዮ 94.3

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

LIVE OFFLINE
Loading...