17.7 C
Ethiopia
Thursday, March 28, 2024

156 የማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ስደተኞች ከካሜሮን ወደ ቀዬአቸው መመለሳቸውን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታወቀ፡፡

ስደተኞቹን ወደ ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ የመመለስ ስራው ከሦሰት ወራት በፊት የተጀመረ ቢሆንም በማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ የተካሄደውን ሀገራዊ ምርጫ ተከትሎ በተቀሰቀሰ የፀጥታ ችግር ምክንያት ስራው ተስተጓጉሎ ቆይቷል ተብሏል፡፡

የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ጉዳይ ኤጀንሲ ይፋ ባደረገው መረጃ መሰረት ህፃናትን ጨምሮ 156 የሚሆኑ ስደተኞች ከዓመታት የስደት ቆይታቸው በኋላ ከካሜሮን ወደ ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ሰላማዊ ቀጣናዎች ተመልሰዋል፡፡

101 የሚሆኑ ስደተኞች ህፃናቶች መሆናቸውም ነው የተገለፀው፡፡እንደ ኤጀንሲው መረጃ ከ2020 በኋላ 5 ሺ የሚሆኑ ስደተኞች ወደ ቀድሞ ቀዬአቸው ተመልሰዋል፡፡

ዘገባው፡- የአናዶሉ ነው፡፡

ቀን 08/08/2013

አሐዱ ራድዮ 94.3

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

LIVE OFFLINE
Loading...