ጥር 15/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በሰሜን ሸዋ ዞን በሞጃና ወደራ ወረዳ ዙብአንባ ቀበሌ ልዩ ቦታው ሞፈር ውሀ ጅረት አካባቢ እየተባለ ከሚጠራው ሥፍራ በደረሰ የትራፊክ አደጋ ሁለት ሰዎች ሲሞቱ አንድ ከባድና አንድ ቀላል ጉዳት መድረሱን የአማራ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

አደጋው ዛሬ ከቀኑ 7 ሰዓት መዳረሻውን መሀልሜዳ ያደረገ ተሸከርካሪ መንገድ ስቶ በመገልበጡ የደረሰ መሆኑ ተነግሯል፡፡

ተጎጂዎች በደብረ-ብርሀን ሪፈራል ሆስፒታል እየታከሙ ሲሆን ፥ የአደጋው መንስኤ እየተጣራ መሆኑን ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡

በዛሬው ዕለት በዚሁ በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን፤ ዳውንት ወረዳ ኩርባ ከተማ መነሻውን ያደረገና ወደ ደሴ ሲጓዝ የነበረ የሕዝብ ማመላለሻ አውቶብስ በደረሰበት የመገልበጥ አደጋ የ25 ሰዎች ሕይወት ማለፉ ይታወቃል።

#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ