በኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ አስረኛ ሳምንት መርሐግብር ስሑል ሽረ ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 0ለ0 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

ጨዋታው 10 ሰዓት ላይ የተደረገ ሲሆ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ተከታታይ ሶስተኛ ጨዋታውን በአቻ ውጤት አጠናቋል።

ስሑል ሽረ ያለፉትን ስምንት ጨዋታዎች ማሸነፍ አልቻለም በሶስቱ ሲሸነፍ በአምስቱ አቻ ተለያይተዋል።

የሊግ ደረጃቸውም

4️⃣ ኢትዮ ኤሌክትሪክ :- 14 ነጥብ
1️⃣7️⃣ ስሑል ሽረ :- 8 ነጥብ


በእለቱ እና በሳምንቱ የመጨረሻ ጨዋታ ሀዲያ ሆሳዕናዎች አራተኛ ተከታታይ ድላቸውን በማስመዝገብ ደረጃቸውን አሻሽለዋል።
በዚህም ነብሮቹ በድል ግስጋሴያቸው ቀጥለዋል።

በኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ አስረኛ ሳምንት መርሐግብር ሀዲያ ሆሳዕና ከአዳማ ከተማ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 2ለ0 በሆነ ውጤት አሸንፈዋል።

የሀዲያ ሆሳዕናን የማሸነፊያ ግቦች ኢዮብ አለማየሁ እና በረከት ወልደዮሐንስ አስቆጥረዋል።

ሀዲያ ሆሳዕና አራተኛ ተከታታይ ድላቸውን አሳክተዋል።

የሊግ ደረጃቸውም

3️⃣ ሀዲያ ሆሳዕና :- 16 ነጥብ
1️⃣2️⃣ አዳማ ከተማ :- 11 ነጥብ

ቀጣይ መርሐግብር

ሰኞ- ሀድያ ሆሳዕና ከ ሲዳማ ቡና
ማክሰኞ - አዳማ ከተማ ከ ወላይታ ድቻ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።