ከፈረንጆቹ 2022 ጀምሮ በሩሲያ እና በዩክሬን መካካል እየተካሄደ ባለው ጦርነት በቅርቡ 'ለሞስኮ ድጋፍ ለማድረግ ነው' በሚል ፒዮንግያንግ ከ12 ሺሕ በላይ የሚደርሱ የልዩ ሃይል አባላቶቿን ልካለች በሚል ክስ ሲቀርብባት ቆይቷል፡፡
እንደዚህ ያሉ ክስ እየቀረበባት የምትገኘው የኪም ጆንግ ኡን ሀገር ሰሜን ኮሪያ ኃላፊነት ሳትወስድ የቆየች ሲሆን፤ አሁን ደግም ወደ ሩሲያ ተልከዋል የተባሉት የጸጥታ ሃይሏቿ በዩክሬን ፕሌኮቮ መንደር በከፈቱት ጥቃት 300 የሚደርሱ ዩክሬናዊያን ገድለዋል ነው የተባለው፡፡
ዓለም አቀፍ የመገናኛ የብዙሃን አውታሮች እንደጠቆሙት ከሆነ፤ ከባለፈው ነሃሴ ወር ጀምሮ በየክሬን በተያዘችው የሩሲያ ከርስክ ግዛት የሰሜን ኮሪያ ወታደሮች ከዩክሬን ጦር ጋር እየተዋጉ እንደሚገኙ ተዘግቧል፡፡
ሩሲያ በዩክሬን ጦር የተያዘችባትን የከርሰክ ግዛት መልሳ ለመቆጣጠር ከ50 ሺሕ በላይ የጦር ሠራዊት አሰማርታ እየተዋጋች መሆኑ የተነገረ ቢሆንም፤ አሁንም ድረስ በርካታ መንደሯቿ በዩክሬን ጦር እንደተያዙባት ተነግሯል፡፡
ከጊዜ ወደ ጊዜ አንድነታቸውን እያጠናከሩ የሚገኙት ሩሲያ እና ሰሜን ኮሪያ፤ እንደ አሜሪካ እና ምዕራብዊያን ያሉ ሀገራትን ስጋት ውስጥ ከቷቸዋል ተብሏል፡፡
በተለየ መልኩ ባለፈው ሰኔ ወር ላይ የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከአቻቸው ከሆኑት ከኪም ጁንግ ኡን ጋር በፒዮንግያንግ የጋራ ወታደራዊ ስምምነት መፈራማቸው የሚታወስ ነው፡፡
በስምምነታቸውም የአንዳቸው የአንዳቸውን የሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት ማክበር ጨምሮ፤ ከሁለቱ አንዳቸው ሀገራት ላይ ጥቃት ከተፈጸመባቸው በጋራ ለመከላከል ከዚህም አልፈው፤ በጋራ ጠላት ላይ የጋራ ወታደራዊ እርምጃ መውሰድ የተካተተበት የመግባቢያ የስምምነት ፊርማ ተፈራርመዋል፡፡
ሰሜን ኮሪያ 300 የሚደርሱ ዩክሬናዊያንን መግደሏ ተገለጸ
ለቭላድሚር ፑቲን አስተዳደር ድጋፍ ለማድረግ ወደ ዩክሬን ግዛቶች የገባው የሰሜን ኮሪያ የልዩ ሃይል ጦር በከፈተው ጥቃት፤ በአንድ መንደር ውስጥ ብቻ 300 የሚደርሱ ዩክሬናዊያንን መግደሉ ተገልጿል፡፡