ጥር 2/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ዓመታዊው የዓለም አቀፉ የስፖርት 'ፎቶግራፊ' ሽልማት አሸናፊዎች በትላንትናው ዕለት ይፋ ተደርገዋል።
በዚህም የኢትዮጵያ አትሌቶች ያሉበት ምስል ሁለተኛ ደረጃን የተሠጠው ሲሆን፤ የብር ሜዳልያንም አስገኝቷል።
በአትሌቲክስ ዘርፍ 'ፎቶግራፈር' ሶና ማልትሮቫ ኢትዮጵያዊያኖቹ አትሌቶች ሰለሞን ባረጋ እና በሪሁ አረጋዊ የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ (ባንዲራ) ለብሰው ተቃቅፈው በመሮጫ ትራኩ ላይ ሲሄዱ ባነሳችው ምስል ነው ማሸነፍ የቻለችው።
ምስሉም የተነሳው በማልትሮቫ ሲሆን፤ ወቅቱም በፓሪስ ኦሎምፒክ ከበሪሁ አረጋዊ የ10,000 ሜትር የብር ሜዳሊያ ስኬት በኋላ ነበር።
6ተኛው ዓለም አቀፉ የስፖርት 'ፎቶግራፍ' ሽልማት 2 ሺሕ 200 ፎቶግራፍ ባለሙያዎችን ከ96 ሀገራት ያሳተፈ ሲሆን፤ ሶና ማልትሮቫ በዚህ ምስል ሁለተኛ በመውጣቷም የብር ሜዳልያ አሸናፊ ሆናለች።