ጉባዔው ኢንጅነር ኃይለኢየሱስ ፍስሐን ፕሬዚዳንት አድርጎ ሲመርጥ ባልተለመደ መልኩ ሁለት ሴት አርቲስቶችን ወደ እግርኳሱ አመራርነት አምጥቷል።

አርቲስት ማስተዋል ወንድወሰን በምክትል ፕሬዚዳንትነት እና አርቲስት ሐረገወይን አሰፋን በአቃቤ ነዋይነት አድርጎ በመሾም ጉቃኤው አነጋጋሪ ውሳኔ ወስኗል።

ፌዴሬሽኑን ለቀጣይ አራት ዓመታት በሥራ አስፈጻሚነት የሚመሩ
ፕሬዘዳንቱን ጨምሮ 9 ሥራ አስፈጻሚዎች በጉባዔተኛው የተመረጡ ሲሆን ከቀድሞው የሥራ አስፈጻሚዎች ጋርም የአርማ ርክክብ አድርገዋል።

ነገር ግን ጉባኤው ከሁሉም በተለየ ሁኔታ የሁለቱ አርቲሥቶች ሹመት በተለይም ደግሞ የማስተዋል ወንዶሰን ነገር የሥፖርቱን ማህበረሰብ ያነጋገረና ያጠያየቀ ሹመት ሆኗል።

በዚህም ፌዴሬሽኑ ለምን አርቲሥት ማሥተዋልን ሾመ? በማለት በማህበራዊ ሚዲያ እና በተለያዬ መንገድ ያልተዋጠላቸውን የግርምት ጥያቄ ሲሰነዝሩ ተመልክተናል።

አዎ ከእስፖርቱ ጋር የሚያገናኛትም ሆነ በስፖርቱ አለም ከዚህ በፊት ያደረገችው ምንም ነገር የለም! የእግር ኳስ ፍቅር እና እውቅት ሊኖራት እንደሚችልኳ የሚያሥረዳ አንዳች ማሥረጃ እስካሁን አልተገኘም።
ይልቅስ በእግር ኳሱ አለም በርካታ አመታትን አስተዋፅኦ ያበረከቱ ፣ እውቀቱ ያላቸው እና በዚሁ የስፖርት ፍቅር ያበዱ ስንት ብቁ ሰዎች እያሉ ይህ የማስተዋል ሹመት ፍፁም ስህተት አይደለም ወይ ሲሉ ጥያቄ አዘል ትችታቸውን አጥብቀው ሰንዝረዋል!

ይሕንን በእግር ኳሱ እንቅስቃሴ ላይ የማትታተወቀውን አርቲስት በምክትል ፕሬዝዳንትነት መሾሙ ለምን ይሆን የሚለውን ትልቅ ጥያቄም
ፌዴሬሽኑ እንደምላሽ የተጠቀመው የአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የፋይናንስ ችግር ስለተስተዋለበት
ይህን የፋይናንስ ችግር ለመቅረፍ ታዋቂ ሰዎችን ወደ አመራር ቦታ በማምጣት የማርኬቲንግ ስራዎችን መስራት የሚለውን አማራጭ በመያዝ
ለአርቲስት ማስተዋል ወንዶሰን የምክትልነት እና ለአርቲስት ሀረገወይን አሰፋ ደግሞ የአቃቤ-ንዋይነት ሹመት ሰጥቻለሁ ብሏል።

እርግጥ ነው ሌሎች ሀገራት ወይም ከተሞች
ታዋቂ ሰዎችን ወደ ፌዴሬሽን ማስጠጋት እና ለማርኬቲንጉ እንዲያገለግሉ ማድረግ እምብዛም ያልተለመደ አይደለም።
ነገር ግን እንደ አማካሪ ወይም አምባሳደር ይሆናሉ እንጂ ምክትል ፕሬዝዳንት ድረስ የደረሰ ስልጣን የተሰጠው አንድም አርቲሥት ስለመኖሩ አስሰን አጥተናል።

እንደአፍሪካ ብቻ ወስደን
የናይጄሪያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንን ብንመለከት
ያላቸውን ታዋቂነት ተጠቅመው ለማርኬቲንጉ ያግዙኛል ብሎ ከሚያስባቸው እውቅ ሙዚቀኞች ጋር በቅርበት ይሰራል፤ ነገር ግን የአመራርነት ሚናን ለአንድም አርቲሥት ሰጥቶ አያውቅም።
የጋና እግር ኳስ ፌዴሬሽንም እውቅ ሙዚቀኛውን " Reggie Rockstone"ንን የቦርድ አባል አድርጎ ሹሞት ያውቃል እንጂ ለሱም ቢሆን ከፍተኛ የአመራርነት ደረጃ አልሰጡትም።

አርቲስቶችን ወደ እግር ኳስም ሆነ ወደ ሌሎች ስፖርታዊ ፌዴሬሽኖች በማስጠጋት ተከታዮቻቸው እንዲነቃቁ የሚደረገው የ' ማርኬቲንግ' ስራ በሌሎች ሀገራትም እንዲሁ አለ።

ትልቁ ነጥብ ግን አርቲስቶቹን የአመራርነት ቦታ ላይ አያስቀምጧቸውም የሚለው ነው። እንኳን በምክትል ፕረዝዳንትነት ይቅርና በቦርድ አባልነትኳ ከስንት አንድ ነው ተፈልጎ የሚገኘው።
ይህም ሊሆን የሚችለው ያ ሠው ለሥፖርቱ ያለው እውቀትና ቅርበት ተገምግሞ ነው።
ነገር ግን የኢትዮጵ ዋና የእግር ኳስ መሠረት የሆነው የመዲናችን ፌዴሬሽን ባልተጠበቀ እና ባልተገመተ ሁኔታ አነጋጋሪ ሹመት ሲሰጥ
ይሄንን ሹመት ከህዝቡ በተጨማሪ ተሿሚዋም ሹመቱ ያልጠበቀችው ስለመሆኑ “ምክትል ፕሬዝዳንት መሆኔን አልጠበቅኩም ነበር" ስትል ተናግራለች።

በዚህ ጉዳይ ዙሪያ ከታዋቂ አርቲሥቶች ይልቅ አንዳንዴ ታዋቂ ባለሀብቶች ወደ አመራርነት ቢመጡ ተቋሙን ከተለያዩ ተቋማት ጋር በፋይናንስ በማስተሳሰር ገቢውን ያሳዳጋሉ በሚል ወደ አመራርነት ሲመጡ ይስተዋላል።

የአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ግን ባልተለመደ መልኩ በማህበራዊ ሚዲያ በርካታ ተከታይ ያላትን ማስተዋል ወንደወሰንን ምክትል ፕሬዝዳንት አድርጎ መሾምን መርጧል።
ማስተዋል የተመረጠችው ባላት የማህበራዊ ሚዲያ ተከታይ ብዛት ብቻ ነው ወይስ.... የሚለው በራሡ ሌላ ጥያቄ ቢሆንም ግን ሹመቱ በራሱ ያልተለመደ እና እንግዳ መሆኑን ከሌሎች ሀገራት ተሞክሮ መረዳት እንችላለን።

ሌሎች ኃገራት እንደዚህ አይነት ራሳቸውን ከሌሎች ሀገራት ጋር በአህጉራዊም ሆነ በአለም አቀፍ ደረጃ ለማፈካከር እና አሸናፊ ለመሆን በቅዲሚያ ሁነኛ ሰዎችን መምረጥ ላይ ትኩረት ያደርጋሉ።

ለዚህም የተመራጩ ፍላጎት ፣ ለስፖርቱ ያለው ፍቅር እና ቅርበት ፣ ለዚህ ሹመት የሚያበቃው ከዚህ በፊት የሠራቸው ስራዎች እና ቢመረጥ ኃላፊነቱን ለመወጣት ምን ያህል ቆራጥነት እንዳለው በፕሮፖዛል ጭምር ለመራጩ አካል በማቅረብ ከሌሎች መመረጥ ከሚፈልጉ ተወዳዳሪዎች ጋር ከፍተኛ ፉክክር አድርጎ በማሸነፍ እንጂ እንዲሁ እንደሎተሪ ባለድል ኃላፊነት ከየትም ተነስቶ ለማንም መሥጠት የተለመደ ጉዳይ አይደለም።

ተመራጩ
ለኃላፊነቱ ያለው ዝግጁነት እና ለሥራው ያለው ቆራጥነት
በሚያቀርበው ፕሮፖዛልና ከዚህ ቀደም በሰራቸው ስራዎች በደንብ ተገምግሞ ሲያበቃ ሹመቱን እንካ ይባላል።

የአዲሥ አበባ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ግን በትላንትናው ሹመቱ እነዚህን ቅድመ ሁኔታዎች ጭራሹንም ከግምት ውስጥ እንዳላሥገባ እና ነገሩን በደንብ ሳያጤን ቀሊል በሆነ መንገድ እንደፈፀመ የሚያሣብቁ አሳማኝ ነገሮችን ማንሳት ይቻላል።

ለምሳሌ ሶስት ነገሮችን ማንሳት ይቻላል።
1ኛ; ምንም እንኳ ከሹመቱ በኋላ ደሥተኛ እንደሆነችና ስራውንም በሚገባ ለመሥራት ቃል ብትገባም ሹመቱን ግን ፈፅሞ ያልጠበቀችው እንደነበረ መግለጿ!

2, አርቲሥት ሰራዊት ፍቅሬ ለአዲሥ አበባ እግር ኳስ ፌደሬሽን ፕረዝዳንትነት እንዲወዳደር ግፋኝ ተሒዶ መጠየቁ
ነገር ግን አልፈልግም የሚል ምላሽ መሥጠቱ ሲሆን

3ኛውና ዋናው ነገር ደግሞ
የፌዴሬሽኑ አቃቤ ነዋይ ሆና የተመረጠችው አርቲስት ሀረገወይን አሰፋ
" መመረጤን ያየሁት ከማህበራዊ ሚዲያ ነው" ማለቷ የምርጫውን ልልነት አመላክቷል።
አርቲስቷ በፌስቡክ የማህበራዊ ትስስር ገጿ ባሰፈረችው መልዕክት “ መመረጤን ያወቅኩት እኔም በማህበራዊ ሚዲያ ተሰራጭቶ ነው “
“ በወዳጆቼ ጥቆማ ወደ ማህበራዊ ሚዲያ ስገባ ተሰራጭቶ ያየሁት መረጃ በፍፁም የማላውቀውና ከሌላው ሰው ዘግይቶ ነበር ያየሁት።" ብላለች።

አርቲስቷ አክላም ስልክ ተደውሎ በፕሮሞሽን፣ መድረክ መምራትና መሰል ጉዳዮች በሙያዋ እንድታግዝ ተጠይቃ እንደነበር አስረድታ