የፓሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩቱ በዘርፉ አደረኩት ባለው ጥናት መሰረት፤ የበይነ መረብ አውታር ግብይቶች የመንግሥት ገቢ ላይ ተፅእኖ እየፈጠሩ መምጣታቸውን አረጋግጫለሁ ብሏል።
በኢትዮጵያ እየተስፋፉ የመጣውን የበይነ መረብ ንግድ ለወደፊቱ በአግባቡ ካልተያዘ በምጣኔ ሐብቱ ላይ አሉታዊ ተፅእኖ መፍጠሩ እንደማይቀር ኢንስቲትዩቱ በጥናቱ ገልጿል።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኢ-መደኛ መልኩ የሚንቀሳቀሱ የበይነ መረብ ነጋዴዎች ተመዝግበው እንዲሰሩ ጥሪ ቢቀርብም፤ የሚመዘገቡና ግብር የሚከፍሉ ነጋዴዎች በቁጥር ደረጃ አነስተኛ መሆናቸውንም ተናግሯል።
በተለይም ከታክስ ስወራ ጋር ተያይዞ ዘርፉ ተግዳሮት እየሆነ መምጣቱን ከግብር ሰብሳቢ መስርያ ቤትን ጨምሮ ከሚመለከታቸው አካላት የተገኘው መረጃ ጥናቱ የዳሰሰበት መሆኑንና፤ ለዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ እንቅፋት ሊሆን ይችላል የሚል እምነት መኖሩን የኢንስቲትዩቱ የምጣኔ ሐብት ተመራማሪ አቶ ሰለሞን አክሊሉ ለአሐዱ ገልጸዋል።
ኢንስቲትዩቱ የበይነ መረብ ንግድን በተመለከተ ለዘርፉ የሕግ ማእቀፍ እንዲዘጋጅ ውትወታ እያደረገ መሆኑንና የፓሊሲ ግብአቶችንም በማቀናጀት ላይ መሆኑን ተናግረዋል።
ከጎረቤት አገራት ጋር ተወዳዳሪ የበይነ መረብ ሕግ እንዲዘረጋና የንግዱ ስርዓትም በዚሁ ልክ እንዲስፋፋ ያስፈልጋል መባሉን የምጣኔ ሐብት ተመራማሪው አቶ ሰለሞን አክሊሉ ለአሐዱ ገልጸዋል።
ጥናቱ በሌሎች አገራት ያለውን ተሞክሮ እየተዘጋጀ መሆኑን ጠቅሰው፤ በአገር ዓቀፍ ደረጃ እየተዘጋጀ ባለው ፓሊሲ ለማካተት ጥረት እየተደረገ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
በኢትዮጵያ የበይነ መረብ ንግድ እየተስፋፋ መምጣቱን ተከትሎ ህግና መመርያ ሊደረግለት መሆኑ እየተነገረ ይገኛል፡፡ ሆኖም ይህ የበይነ መረብ ንግድ በትክክል ግብር የሚከፍሉ የንግድ ማሕበረሰቦች ላይ አሉታዊ ተፅእኖ እያሳደረ መሆኑ ተነግሯል።
ከውጭ አገራት የሚገቡ የምርቶች ጥራት ጉዳይ ያልተረጋገጡ በመሆናቸው በተጠቃሚው ላይ ተፅእኖ እየፈጠሩ መሆናቸውን በፓሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት በጥናቱ አሳስቧል።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ያልተረጋገጡ መድኃኒቶች እየተበራከቱ መሆናቸውን ጠቅሶ፤ በሕብረተሰቡ ጤናን ጨምሮ አጠቃላይ ማሕበረ- ኢኮኖሚያዊ ቀውስ እየፈጠሩ እንደሚገኙም አደረኩት ባለው ዳሰሳ አመላክቷል።
ኢ-መደበኛ የበይነ መረብ ነጋዴዎች ወደ መደበኛው የንግድ ስርዓት እንዲመጡና ከሚመለከተው የመንግሥት መስርያቤት ፍቃድ ወስደው እንዲሰሩ የሕግ አካላት የበኩላቸውን ማድረግ ይኖርባቸዋል ሲል ኢንስቲትዩቱ አሳስቧል።
እየተስፋፋ የመጣው የበይነ መረብ ንግድ በምጣኔ ሐብቱ ላይ አሉታዊ ተፅእኖ እያሳደረ መምጣቱን ተገለጸ
ሕዳር 23/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በኢትዮጵያ እንደቴሌግራም፣ ኢንስታግራምና ፌስቡክ በመሳሰሉት የበይነ መረብ አውታሮች በመጠቀም የሚሸጡ የሚለውጡ ነጋዴዎች እየተበራከቱ መምጣታቸውን ተከትሎ፤ ከግብይቶች መንግሥት ማግኘት ያለበትን ታክስ እያሳጡት መሆኑን የፓሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት አስታውቋል።