መጋቢት 30/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የሙዚቃ ባለሙያው ካሙዙ ካሳ "የኢትዮጵያ የባህል ድልድይ ሕዝብ ለሕዝብ ትስስር" በሚል መሪ ቃል በሚካሄደው ዝግጅት ላይ፤ የኢትዮጵያ የባህል ዕሴቶች እና ኪናዊ ፀጋዎች ለብሪክስ አባል ሀገራት ሊያስተዋውቅ መሆኑ ተነግሯል፡፡
ኢትዩጵያ ከብሪክስ አባል ሀገራት ጋር በዲፕሎማሲው መስክ ከምትሰራቸው ሥራዎች አንዱ የባህልና የኪነ ጥበብ ዲፕሎማሲ እንደመሆኑ፤ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር በዚህ ልክ አቅዶ እየሰራ እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡
በዚህም “የኢትዮጵያ የባህል ድልድይ ሕዝብ ለሕዝብ ትስስር” በሚል መሪ ቃል ኢትዩጵያ ላይ ያሉ ቱባ ባህላዊ ዕሴቶችን፣ ኪናዊ ፀጋዎችን እንዲሁም የፈጠራ ምርቶችን በመጠቀም ከኢትዩጵያ ከተለያዩ አካባቢዎች በተውጣጡ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች ለብሪክስ አባል ሀገራት ለማቅረብ ዝግጅት መጀመሩን ገልጿል፡፡
ይህንን ዝግጅት ለማቅረብም የሚያስችል የውል ስምምነት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከሻኩራ ፕሮዳክሽን ጋር መፈራረሙን ነው፤ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር በማህበራዊ ትስስር ገጹ ያስታወቀው፡፡
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ