መጋቢት 8/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በማይናማር በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ ተጨማሪ 53 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ማድረጉን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ኢትዮጵያኑ ከማይናማር እገታ ወጥተው ታይላንድ ወታደራዊ ካምፕ የነበሩ ሲሆን፤ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር በመተባበር ወደሀገራቸው ተመልሰዋል።

በዚህም በአካባቢው ከሚገኙ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ጋር በመነጋገር ትናንት 23 ዜጎችን እንዲሁም፤ ዛሬ 30 ዜጎች በአጠቃላይ በካምፑ የነበሩት 53 ዜጎች እንዲመለሱ መደረጉን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

እስካሁን ከማይናማር እገታ ወጥተው ታይላንድ ወታደራዊ ካምፕ የነበሩ በመጀመሪያውና ሁለተኛው ዙር በጠቅላላው 130 ዜጎችን መመለስ መቻሉም ተገልጿል።

#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ