የካቲት 16/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ከተለያዩ አካባቢዎች የሚመጡ ተማሪዎች ያለምንም የጸጥታ ችግር ትምህርታቸውን እንዲያጠናቅቁ ከከተማ መስተዳድሩ ጋር እየሰራ እንደሚገኝ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ አስታውቋል፡፡
ዩኒቨርስቲው ከሚያጋጥሙት ችግር እየተማረ ተማሪዎችን ከፀጥታ ችግር ቀድሞ የመከላከልን ሥራ እየሰራ እንደሚገኝ ጠቁሟል።
ከዚህ ቀደም የተለያዩ ፍላጎቶችን ለማስፈጸም ዩኒቨርሲቲዎችን ለግጭት ማዕከል እንዲሆኑ የተለያዩ አካላት ሲጠቀሙባቸው ነበር የሚሉት የዩኒቨርስቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር አስራት አጸደወይን ናቸው፡፡
ለዚህም ዩኒቨርስቲው የተለያዩ የተማሪዎች አደረጃጀቶች በማጠናከር እንዲሁም ከከተማው መስተዳድር ጋር በጋራ በመስራትና ከጸጥታ አካላት ጋር ያለንን ግንኙነት በማጠናከር ለሰላም እና ጸጥታ መደፍረስ መንስዔ ሊሆኑ የሚችሉ ችግሮችን እየተከላከልን ነው ብለዋል።
ከዚህ ጋር ተያይዞ እስካሁን በተማሪዎችም ሆነ በዩኒቨርስቲው አካላት ላይ የከፋ ጉዳትም ሆነ አለመግባባት ተፈጥሮ እንደማያውቅ ተናግረዋል።
አክለውም አሁን ያለው ነባራዊ ሁኔታ ለግጭት ትኩረት የሚስብ ቢሆንም፤ ዩኒቨርስቲው ካለዉ ነባራዊ ሁኔታ አንፃር ቅድመ ዝግጅት በማድረግ እየተሰራ መሆኑን አብራርተዋል።
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የግጭት ማዕከል እንዳይሆን ከከተማው መስተዳድሩ ጋር እየሰራ መሆኑን ገለጸ
