በኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ 10ኛ ሳምንት መርሐግብር ኢትዮጵያ ቡና ከአርባምንጭ ከተማን 2-0 በረቱበት ጨዋታ ላይ ግቦቹን ዲቫይን ዋቹኩዋ እና ኦካይ ጁል ማስቆጠር ችለዋል።
ኢትዮጵያ ቡና ከሶስት ጨዋታዎች በኋላ ወደ ድል መመለስ ችለዋል።
የሊግ ደረጃቸው
9️⃣ ኢትዮጵያ ቡና :- 11 ነጥብ
1️⃣3️⃣ አርባምንጭ ከተማ:- 10 ነጥብ
በተጨማሪም
በኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ አስረኛ ሳምንት መርሐ ግብር ባሕርዳር ከተማ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር ያደረጉትን የዕለቱን የ1 ሰዓት ጨዋታ 3ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።
የጣና ሞገዶቹን የማሸነፊያ ግቦች ፍሬው ሰለሞን ፣ ጄሮም ፍሊፕ እና ሙጂብ ቃሲም በፍጹም ቅጣት ምት አስቆጥረዋል።
ባሕር ዳር ከተማ ያለፉት አምስት ጨዋታዎች አልተሸነፉም ሶስቱን ሲያሸንፉ በሁለቱ አቻ ተለያይተዋል።
የሊግ ደረጃቸው
2ኛ ባሕር ዳር ከተማ :- 17 ነጥብ
15ኛ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ :- 8 ነጥብ