በትላንቱ ቀዳሚ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ መርሐግብር ስሑል ሽረ እና ኢትዮ ኤሌክትሪክ ጨዋታቸውን ነጥብ በመጋራት ፈጽመዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባዔውን ትላንት ያካሄደ ሲሆን የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ምርጫን ጨምሮ በአራት አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ አፅድቋል።
ሕዳር 25/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የቀድሞ ተዋጊዎችን ወደ ማህበረሰቡ ለመቀላቀል እየተሰራ ያለው ሥራ መቀጠሉን የገለጸው የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን፤ በትግራይ ክልል ወደ ማህበረሰቡ ለመቀላቀል ካሰባቸው 70 ሺሕ በላይ የቀድሞ ተዋጊዎች መካካል 2 ሺሕ ገደማ የሚሆኑት በማዕከሉ ስልጠና መውሰዳቸውን ገልጿል፡፡
ሕዳር 25/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ብሔራዊ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን፤ በአገር ውስጥ ተፈናቃዮች ዙሪያ ከተለያዩ ረጂ ተቋማት የሚወጡ መረጃዎች መሬት ላይ ካለው ሀቅ ጋር አይገናኙም ሲል ለአሐዱ ገልጿል።
ሕዳር 25/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ሕገወጥ የነዳጅ ግብይትን ይገታል የተባለለት ከ 300 ሺሕ እስከ 700 ሺሕ ብር የገንዘብ መቀጮ ያለው ሕግ ወጥቶ፤ ባለፈው ሳምንት ጀምሮ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቅረቡን የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን አስታውቋል።
👉 "ከደረሰኝ ጋር ቁጥጥር እያደረገ የሚገኘው ገቢዎች ቢሮ ነው" ንግድ ቢሮ
ሕዳር 25/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ኢትዮጵያ የንጥረ ነገር እጥረት በጤና ላይ የሚያስከትለውን ችግር ለማከም እና ለመርዳት ብቻ፤ በዓመት ከአጠቃላይ ኢኮኖሚው ላይ 5 ቢሊየን ዶላር እንደምታጣ ሚለር ፎር ኒውትሬሽን ኢትዮጵያ ገለጸ።
ኤፍ ኤም 94.3