መጋቢት 8/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለቪ.አይ.ፒ (VIP) እና ልዩ ቻርተር በረራ አገልግሎት መስጠት የሚያስችለውን የመጀመሪያውን ቦይንግ 737-800 ቢዝነስ አውሮፕላን መረከቡን አስታውቋል፡፡
ይህ የቢዝነስ አውሮፕላን በተለይም በአፍሪካ የንግድና ኢንቨትመንት ሥራዎቻቸውን ለማሳለጥ በርካታ ጉዞዎችን ለሚያደርጉ በከፍተኛ ንግድ ሥራ ላይ ለተሰማሩ ግለሰቦች፣ ድርጅቶች እና ደረጃውን የጠበቀ ልዩ ልዩ የቻርተር በረራ አገልግሎት ለሚሹ ተጓዦች በሙሉ አየር መንገዱ ልዩ አገልግሎት እንዲሰጥ ያስችለዋል ተብሏል።
በአቀባበል ሥነ-ስርዓቱ ላይ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከፍተኛ አመራሮች ፣ የቦይንግ ኩባንያ ተወካዮች እና ጥሪ የተደረገላቸው ተወካዮች መገኘታቸውን ከአየር መንገዱ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
አየር መንገዱ ለቪ.አይ.ፒ እና ልዩ ቻርተር በረራ የሚያገለግል ቦይንግ 737-800 ቢዝነስ አውሮፕላን ተረከበ
