የካቲት 12/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) 88ኛው የየካቲት 12 የሰማዕታት መታሰቢያ በአዲስ አበባ ስድስት ኪሎ የሰማዕታት ሐውልት በመከበር ላይ ይገኛል።
በመታሰቢያ ሥነ ስርዓቱ ላይ አቡነ እንጦስ የምስራቅ ሀረርጌ ሀገር ስብከት እና የሲኖዶስ አባል፣ የአዲስ አበባ ባህል፣ ኪነጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ሂሩት ካሳው (ዶ/ር)፣ የጥንታዊ ጀግኖች አርበኞች ማህበር ፕሬዝዳንት ልጅ ዳንኤል ጆቴ መስፍን፣ የሐይማኖት አባቶች እንዲሁም አርበኞችና ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

ዕለቱ ፋሽስት ጣሊያን ከየካቲት 12/1929 ዓ.ም ጀምሮ ለ3 ተከታታይ ቀናት ከ33 ሺሕ በላይ በአዲስ አበባ እና በዙሪያዋ በነበሩ ንፁሃን ዜጎችን በአሰቃቂ ሁኔታ በጅምላ ተገደለበትን ቀን በማሰብ የሚከበር ነው።

በመታሰቢያ ሥነ-ስርዓቱም ላይም የህሊና ጸሎት የተደረገ ሲሆን፤ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና የኢትዮጵያ ጥንታዊት ጀግኖች አባት አርበኞች በየካቲት 12 ሰማዕታት መታሰቢያ ሐውልት ሥር የአበባ ጉንጉን አስቀምጠዋል።
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ