ጥር 30/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር 01 ቀበሌ በሮቢ የትንባሆ እርሻ ልማት ድርጅት ውስጥ የነበረና በሥራ ላይ የነበሩ አራት ግለሰቦች ላይ ነብር ጉዳት ማድረሱን የከተማ አስተዳደሩ አስታውቋል፡፡

ነብሩ ጥቃቱን ካደረሰ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ በጥይት መገደሉም ነው የተነገረው፡፡

ጉዳት የደረሰባቸው አራቱ ግለሠቦችም በሸዋሮቢት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የሕክምና እርዳታ እየተደረገላቸው መሆኑ ተገልጿል።

#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ