ጥር 30/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በጋምቤላ ክልል በሙቀት መጨመር ምክያት የመንግሥት ከነገ ጀምሮ የሥራ ሰዓት ለውጥ እንደሚደረግ የክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት አስታውቋል።
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኡቶው ኡኮት፤ "በክልሉ የሙቀቱ መጨመር ለሥራ ምቹ ባለመሆኑ ከነገ የካቲት 1 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ለሦስት ወራት የሚቆይ የሥራ ሰዓት ለውጥ ይደረጋል" ብለዋል።
በዚህም መሰረት ቀደም ሲል ከጠዋቱ 1፡00 እስከ 6፡30 የነበረው የመደበኛው የሥራ ሰዓት፤ ከ1፡00 እስከ 5፡30 እንደሚሆን ተናግረዋል፡፡
እንዲሁም ከሰዓት በኋላ ከ9፡00 እስከ 11፡30 የነበረው የሥራ ሰዓት፤ ከ10፡00 እስከ 12፡30 እንዲሆን መወሰኑን አስታውቀዋል፡፡
ይህ የሥራ ሰዓት ለውጥ በማጃንግ ዞን የመንገሺና ጎደሬ ወረዳዎችን እንደማይጨምር ተገልጿል፡፡
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
በጋምቤላ ክልል ከነገ ጀምሮ የሥራ ሰዓት ለውጥ እንደሚደረግ ተገለጸ
