የካቲት 14/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የኢትዮጵያን አዲስ የኤሌክትሮኒክስ ፓስፖርት ዛሬ የካቲት 14 ቀን 2017 ዓ.ም ይፋ አድርጓል።

አገልግሎቱ ይፋ ያደረገው አዲስ ፓስፖርት በጃፓኑ ቶፓን ሴኩሪቲ ኢትዮጵያ አማካይነት ዘመኑ በደረሰበት ምስጢራዊ ኅትመት የታተመ ስለመሆኑ የተገለጸ ሲሆን፤ የአንድን ግለሰብ ባዮሜትሪክ መረጃ ጨምሮ የጣት አሻራዎችን፣ የፊት ለይቶ ማወቂያ እና የኤሌክትሮኒክስ ቺፕስ ያካተተ መሆኑ ተነግሯል።

Post image

በዛሬው ዕለት በሳይንስ ሙዚየም የተዋወቀው ይህ ፖስፖርት በገጾቹ ላይ የሀገር ገፅታ የሚያስተዋውቁ የኢትዮጵያ መለያ ምስሎችንያካተተ ሲሆን፤ ሀሰተኛ መረጃዎችን እና ማጭበርበርን ለመከላከል የሚያስችል የላቀ የደህንነት ባህሪያትን መያዙም ተገልጿል።

Post image

አዲሱ ፓስፖርት ደህንነቱ የተጠበቀ፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ የተቀመጡ መመዘኛዎች ያሟላና ዓለም አቀፍ ተቀባይነትን ያረጋገጠ ስለመሆኑም የተነገረ ሲሆን፤ በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኘው የለሚ ኢንደስትሪያል ፓርክ የሚመረት መሆኑም ተመላክቷል፡፡

#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ