የካቲት 14/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በኢትዮጵያ አየር ኃይል የተሰራችው ፀሐይ - 2 የስልጠና አውሮፕላን የመጀመሪያ የሙከራ በረራዋን በስኬት ማከናወኗ ተገልጿል፡፡

ፀሐይ -2 አውሮፕላን ለበረራ ማሰልጠኛ እና ለሌሎች አገልግሎት መዋል የምትችል ሲሆን፤ የተሰጣትን ግዳጅ በብቃት መፈፀም የሚያስችላትን የዘመኑን የአቪዬሽን ቴክኖሎጂ መታጠቋ ተነግሯል፡፡

Post image

የአውሮፕላኗ ስኬታማ የሙከራ በረራ አየር ኃይሉ የደረሰበትን የከፍታ ጉዞ እንደሚያሳይ መሆኑን የመከላከያ ሠራዊት በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባሰፈረው መረጃ አመላክቷል፡፡

በቀጣይነት ወደ ምርት ሂደት ለመሸጋገር ፋብሪካውን የማደራጀት፣ የመፈተሻ እቃዎችን የማሟላትና የሞያተኞችን አቅም የማጎልበት ሥራ በመከናወን ላይ መሆኑ ተገልጿል፡፡

Post image

የትራንስፖርት አውሮፕላን ስኳድሮን አዛዥና አብራሪ እንዲሁም የፀሃይ -2 የሙከራ በረራን በስኬት ያካሄዱት ሻለቃ ፍቃዱ ደምሴ፤ አውሮፕላኗ የበረራ አቅሟ አስተማማኝና ተቋሙ ለያዘው የወደፊት ራዕይ ጉልህ አስተዋፅኦ የምታበረክት መሆኗን ገልጸዋል፡፡

#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ