ኢትዮጵያ ከጎረቤት ሀገራት የሚመጣባትን የፀጥታ ስጋት ለመከላል በየትኛውም ሁኔታ ቢሆን እራሷን የመጠበቅ ህጋዊ መሰረት አላት ተባለ፡፡

የሶማሊያ መከላከያ ሚኒስትር በቅርቡ የአፍሪካ ህብረት ሰላም አስከባሪ ሆኖ እንደ አዲስ በሚቋቋመው ስብስብ ውስጥ #የኢትዮጵያ_ሰራዊት አይኖርም ማለታቸው የሚታወስ ሲሆን በዚህ ነጥብ ዙሪያ የውጪ ጉዳይ መ/ቤት ማብራሪያ ተጠይቆ ምላሽ ሰጥቷል፡፡

የሚኒስትሩ ቃል አቀባይ አምባሳደር ነቢያት ለጥያቄው በሰጡት ምላሽ የኢትዮጵያ ሰራዊት ለ #ሶማሊያ ሀገር መሆንና መረጋጋት የከፈለውን ዋጋ አለም ያውቀዋል፤ ስጋት እስከማይሆንበት ደረጃ እስኪደርስም ኢትዮጵያ ትግሏን ትቀጥላለች ብለዋል፡፡

የኔነህ ሲሳይ