የካቲት 4/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በ38ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ እንዲሁም 46ኛው የሕብረቱ የሥራ አስፈጻሚ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ላይ ለመሳተፍ፤ ወደ መዲናዋ አዲስ አበባ ከተማ ከተለያዩ የአፍሪካ ብሎም ዓለም አገራት እንግዶች በመግባት ላይ ይገኛሉ፡፡

በዚህም ምክንያት ከዛሬ የካቲት 04 ቀን 2017 ዓ.ም ከንጋቱ 12:00 ጀምሮ እስከ የካቲት 09 ቀን 2017 ዓ.ም ማታ 12:00 ድረስ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ፤

👉 በኤሌክትሮኒክ ታክሲ ስርዓት(ኤታስ) አገልግሎት የሚሰጡ፣

👉 የሜትር ታክሲ፣

👉 የላዳ፣ የታክሲ እና መሰል ተሽከርካሪዎችን የምታሽከረክሩ አሽከርካሪዎች በኮሪደር ልማት በለሙና የእንግዶች መተላለፊያ በሆኑ መንገዶች ላይ ለአጭር ደቂቃም ሆነ ለሰዓት በመንገድ ዳር መቆም የማይቻል መሆኑን የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ አስታውቋል።

#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ