ጥር 28/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የሩሲያ ወታደራዊ ኃይል በምስራቅ ዩክሬን እያካሄደ ባለው ጥቃት ተጨማሪ ሁለት ሰፈሮችን መቆጣጠሩን ገልጿል።

የሩስያ የመከላከያ ሚኒስቴር በዛሬው ዕለት ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው፤ በሰሜን ምስራቅ ካርኪቭ ክልል ውስጥ በሞስኮ ጥቃት ውስጥ ትልቅ ግንባር ከሆነው ኩፒያንስክ ከተማ በሰሜን ምስራቅ 21 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኘውን የኖቮምሊንስክን መንደር መያዙን አስታውቋል።

በተጨማሪም በዶኔትስክ ግዛት በተከፈተው ጥቃት ቁልፍ የሆነችውንና ከፖክሮቭስክ ከተማ በስተምስራቅ 26 ኪ.ሜ. ርቀት ላይ የምትገኘው ባራኒቪካ መንደርን መቆጣጠሩን ገልጿል።

ሩሲያ ከቅርብ ወራት ወዲህ በተለይም በዶኔትስክ ክልል፣ በፖክሮቭስክ አካባቢ ውጊያው በተጠናከረባቸው አካባቢዎች መንደሮችን እየረቆጣጠረ እንደሚገኝ በተደጋጋሚ እየተነገረ ይገኛል፡፡

ከተማዋ በክልሉ ላሉ የዩክሬን ጦር ኃይሎች ወሳኝ የሎጂስቲክስ ማዕከል ሆና የሚያገለግል ሲሆን፤ ዩክሬን ከሩሲያ ጋር ድንበር የሚትጋራበት ቦታ መሆኑን የአናዶሉ ዘገባ አመላክቷል።

ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ በዩክሬን በኩል የተባለ ነገር የለም፡፡

#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ