የካቲት 14/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ካርጎና ሎጂስቲክስ አገልግሎት የ2025 የአፍሪካ ምርጥ የካርጎ አየር መንገድ ሽልማት ማሸነፉን አስታውቋል፡፡

አየር መንገዱ በኬንያ ናይሮቢ በተካሄደው "የSTAT ታይምስ ዓለም አቀፍ የአየር እቃ ጭነት አገልግሎት ልሕቀት ሽልማት " መርሃ ግብር ላይ ነው፤ የዓመቱ የአፍሪካ ምርጥ የካርጎ አየር መንገድ በመባል ሽልማትን ያገኘው፡፡

ከዚህ በተጨሪም በመድረኩ ከዚህ በተጨማሪም "የአፍሪካ ምርጥ የካርጎ አገልግሎት ኤርፖርት" እና "ፈጣን ዕድገት እያስመዘገበ ያለ የዓመቱ የካርጎ አገልግሎት አየር መንገድ" በመባል ተደራራቢ ዕውቅና እና ሽልማት ማግኘቱን አስታውቋል፡፡

እነዚህ ሽልማቶች የኢትዮጵያ አየር መንገድ ካርጎና ሎጂስቲክስ አገልግሎት እየሰጠ ላለው ዘርፈ ብዙ ዓለም አቀፍ አገልግሎት አስተማማኝነትና ቅልጥፍና ማረጋገጫዎች መሆናቸውን አየር መንገዱ ገልጿል፡፡

#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ