የካቲት 17/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን አራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 ኢስት አፍሪካ ሆልዲንግ ሼር ካምፓኒ በኮሪደር ልማት በተሠራ አስፓልት ላይ ኃላፊነት በጎደለው ሁኔታ በማቆሸሹ በደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኦፊሠሮች 300 ሺሕ ብር መቀጣቱን አስታውቋል፡፡

Post image


ድርጅቱ በተደጋጋሚ ግንዛቤ ተፈጥሮለት ከዚህ በፊት 100 ሺሕ ብር የተቀጣ ሲሆን፤ ድጋሚ ተመመሳሳይ ጥፋት በመፈጸሙ የቅጣቱ እጥፍ 200 ሺሕ ብር በድምሩ 300 ሺሕ ብር መቀጣቱ ነው የተገለጸው።


Post image


የአዲስ አበባ የደንብ ማስከበር ባለስልጣን በደንብ ተላላፊዎች ላይ የሚወስደውን እርምጃ አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑ በመግለጽ፤ የከተማዋ ነዋሪ አጥፊዎችን መረጃ በመስጠት የጀመረውን ጥቆማ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪውን አቅርቧል።

#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ