የካቲት 3/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 ምሽትን ተገን በማድረግ የቆሸሸ ውሃ አዲስ ወደ ተሠራው አስፓልት የለቀቀው የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት 300 ሺሕ ብር መቅጣቱን አስታውቋል።

ከገንዘብ ቅጣቱ በተጨማሪም ያቆሸሸውን አካባቢ እንዲያጸዳ መደረጉን ባለስልጣኑ ገልጿል፡፡
ባለስልጣኑ የህብረተሰቡ የጋራ ሀብት የሆኑ የኮርደር ልማትና በሌሎች አካባቢ የሚገኙ መሠረተ ልማቶችን፣ ለሕዝብ የተሰሩ አረንጓዴ ስፍራዎች እና የወንዝ ዳርቻ ፕሮጀክቶችን ደህንነት በመጠበቅ እንዲገለገል መልዕክቱን አስተላልፏል ፡፡
አክሎም በከተማዋ ደንብ የሚተላለፉ የግልና የመንግሥት ድርጅቶች እና ግለሰቦች ላይ የሚወስደውን እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል።
ባለስልጣኑ ህብረተሰቡ ለማንኛውም የደንብ መተላለፎች መረጃ በ9995 ነፃ የስልክ መስመር ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪውን ማቅረቡን የባለሥልጣኑ ኮሙዩኒኬሽን መረጃ አመላክቷል፡፡
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ