የካቲት 4/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በመዲናዋ የሚካሄደው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ የሞተር ሳይክል እንቅስቃሴ ተከልክሏል።

ከዛሬ የካቲት 04 ቀን 2017 ዓ.ም ከዚህ ሰዓት ጀምሮ እስከ የካቲት 09 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ በመዲናዋ በየትኛውም አካባቢ ሞተር ሳይክል ማሽከርከር የማይቻል መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ አስታውቋል፡፡

#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ