መጋቢት 11/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በፌዴራል መንግሥት የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት የአፈፃፀም ሪፖርትን መነሻ በማድረግ፤ ከምክር ቤት አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎችና አስተያየቶች ምላሽ እና ማብራሪያ እየሰጡ ይገኛሉ።

በዚህም የኢትዮጵያ የባለፈው ዓመት ኢኮኖሚ እድገት 8 ነጠብ 1 በመቶ መሆኑን ያስታወሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ "በተያዘው በጀት ዓመት ከ8 ነጠብ 4 በመቶ በላይ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል" ሲሉ ገልጸዋል።

"ከአምስቱ ዘርፎች አንዱ የሆነው ግብርና ለኢኮኖሚው ሰፊ የሆነ ድርሻ አለው" ያሉም ሲሆን፤ በአነስተኛ ግብርና ባለፈው ዓመት ከነበረው 17 ነጠብ 5 ሚሊየን ሄክታር ዘንድሮ 20 ነጠብ 5 ሚሊየን ሄክታር መሬት በምርት መሸፈኑን አንስተዋል።

እንዲሁም በኩታ ገጠም ግብርና ባለፈው ዓመት 8 ነጠብ 7 ሚሊየን ሄክታር መሬት በምርት ሲሸፈን ዘንድሮ ወደ 11 ነጠብ 6 ሚሊየን ሄክታር ከፍ ማለቱን አክለው ገልጸዋል፡፡

ከአፍሪካ በስንዴ ምርት ከአፍሪካ በከፍተኛ ደረጃ ላይ መቀመጧን ገልጸው፤ በመህር ወቅት 4 ነጠብ 2 ሚሊየን ሄክታር ሲሸፈን በበጋ 3 ነጠብ 5 ሚሊየን ሄክታር መሬት በስንዴ ምርት መሸፈኑ አንስተዋል።

ሆኖም በስንዴት ምርት የተገኝዉ ውጤት ላይ "የሚያማቸው፣ የሚቃጥላቸው እና የሚያቀረሻቸው ቢኖሩም እውነታው ይሄ ነው" ብለዋል።

ግብርናው መሻሻሉን ማሳያ ከዚህ ቀደም በሴፍቲኔት ተጠቃሚ የሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች እያረሰ ራሱን መቻል መጀመራቸውን ጠቁመዋል።

#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ