መጋቢት 11/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በኢትዮጵያ እ.ኤ.አ ከ2015 ጀምሮ ምግብ፣ በቤትና በግል እንክብካቤ ምርቶችን አቅራቢ ከሆኑ ድርጅቶች ውስጥ ግንባር ቀደም ተቋም የሆነው ዩኒሊቨር ኢትዮጵያ በሲግናል ብራንድ አማካኝነት ከኢትዮጵያ የጥርስ ሐኪሞች ማህበር እና ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የዓለም የአፍ ጤና ቀንን አክብሯል።

ዩኒ ሊቨር ለግል እና የጋራ ንጽህና መጠበቅ ካለው ቁርጠኝነት በመነሳት የሲግናል የጥርስ ሳሙና የአፍ ደህነት እንዲጠበቅ የሚያግዝ የግንዛቤ ማስጨበጫ በመላው ዓለም ለሚገኙ በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ልጆች በማዳረስ ጥርስን መፋቅ የዘወትር ተግባር እንዲሆን እየሰራ እንደሚገኝ አስታውቋል።

Post image

በኢትዮጵያ ሲግናል "ቀን እና ማታ ጥርስን መፋቅ "በተሰኘ ንቅናቄ አማካኝነት፤ የጥርስ መፋቅን ልማድ ለማዳበር የሚያስችሉ የግንዛቤ ማስጨበጫ ተግባራትን ሲያከናውን መቆየቱ ተጠቁሟል።

በዚህ ግምትም ይህንን ተግባሩን አጠናክሮ በመቀጠል ከአጋር አካላት ጋር በመሆን ተማሪዎችንና ማህበረሰቡን ማዕከል ያደረጉ ንቅናቄዎችን አስጀምሯል።

የሲግናል የጥርስ ሳሙና ብራንድ ተልዕኮ ዋና ማጠንጠኛ ዘላቂ የንጽሕና አጠባበቅ ልማድ ማድረግ እንደሆነም ገልጿል።

በንቅናቄ ማስጀመሪያ ወቅት መልዕክት ያስተላለፉትየዩኒ ሊቨር ኢትዮጵያ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ጆርጅ ኦሱ አንሳሕ፤ በጥራት የላቁ ምርቶችን ከማምረት ባሻገር የአፍ ጤና አጠባበቅ እንዲዘወተር ጥረት እያደረገ መሆኑን አብራርተዋል።

ነጻ የአፍ እና ጥርስ ምርመራ እንዲሁም በባለሙያዎች የሚሰጥ እና ምክር የዘንድሮው የዓለም ጤና ቀንን አስመልክቶ ከሚከናወኑ ተግባራት መካከል እንደሚጠቀስም ዳይሬክተሩ ለአሐዱ ተናግረዋል።

ይህ ንቅናቄም በተያዘው ወር በ288 ትምህርት ቤቶች በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ተማሪዎች ተደራሽ እንደሚያደርግ ተገልጿል።

በዓለም ላይ ከ120 ዓመታት በላይ በሥራ ላይ የቆየው ዩኒሊቨር ሲግናል፣ ላይፉ ቦይ ሳሙና፣ ሰንላይት፣ ክኖር አንኳር ስንላይት ሳሙናና ዱቄት እንዲሁም ላክሲ ጨምሮ ከ 400 በላይ ምርቶችን ያመርታል፡፡

ተቋሙ በኢትዮጵያ ከ9 ዓመታት በላይ ምርቶችን ለገበያ ሲያቀርብ የቆየ ሲሆን፤ ከ20 በላይ ምርቶች ለሀገር ውስጥ ገበያ እንደሚያቀርብ ገልጿል።

#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ