ጥር 1/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ትምህርት ሚኒስቴር ከታሕሳስ 1 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በየትኛውም የከፍተኛ ትምህርት ተቋም የተሰጠ እና የሚሰጥ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ዕድገት ተቀባይነት እንደማይኖረውም መግለጹ ይታወቃል፡፡

ለዚህም ዕግዱ ምክንያትም ከጥቅምት 4 ቀን 2013 ዓ.ም. ጀምሮ በሥራ ላይ የነበረው፤ "የአካዳሚክ ሠራተኞች የደረጃ ዕድገት መመሪያ" በመሻሻል ላይ እንደሆነ ገልጿል።

አሐዱ ያነጋገራቸው በትምህርት ሚኒስትር ከፍተኛ ልማት ዘርፍ ዴኤታ የሆኑት ኮራ ጡሹኔ፤ "ትምህርት ሚኒስቴር ከሚያወጣው ደረጃ በታች መሆን አይቻልም" ብለዋል፡፡

አክለውም መመሪያ የማክበር ችግር እንዲሁም መመርሪያው ራሱ ክፍተቶች ያሉበት መሆኑን ጠቁመዋል። በቅርቡም ያለው ችግር ተፈቶ እገዳው እንደሚነሳ ተናግረዋል፡፡

ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በደረሰው ጥቆማ መሰረት ትምህርት ሚኒስቴር ባደረገው ማጣራት፤ ከመመሪያው በታች የፕሮፌሰር ማዕረግ እየሰጡ መሆኑን ማረጋገጡን ገልጸዋል።

ትምህርት ሚኒስቴር ለሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቁማት በላከው ደብዳቤ ዕግዱ ከወጣ በኋላም መመምሪያውን ባልተከተለ፣ ግልጽነት በጎደለው፣ ወጥነት በሌለው እና ከትምህርት ጥራት ማስጠበቂያ አሰራሮች በሚጣረስ መልኩ የፕሮፌሰርነት ዕድገት መስጠት መቀጠላቸውን ገልጾ እንደነበር ይታወሳል።

ዕግድ ባልተነሳበት ሁኔታ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለ5 ሙሁራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ዕድገት መስጠቱን ማስታወቁ አይዘነጋም።

ዩኒቨርሲቲው የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ዕድገቱን የሰጠው በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ''ስለ ራስገዝ ዩኒቨርሲቲ ለመደንገግ በወጣው'' አዋጅ ቁጥር 1294/2015 መሠረት መሆኑን አስታውቋል፡፡