"በአካባቢው መረረጋጋት እና ትብብር እንዲመጣ እንሰራለን" ያሉም ሲሆን፤ ኤርትራ ኢትዮጵያን ከሚጎዱ ሀገራት ጋር ትሰራለች መባሉን አስተባብለዋል፡፡

ይህንን የፕሬዝዳንቱን ንግግር በሚመለከት አሐዱ ያነጋገራቸው የፖለቲካ ሳይንስ መምህሩ አቶ ጥላሁን ሊበን፤ "ለሁሉም ነገር ኢትዮጵያ ቅድሚያ የውስጥ ችግሯን መፍታት እንዳለባት ብዙዎችን የሚያስማማ ነው" ብለዋል፡፡

"የፕሬዝዳንቱን ሀሳብ እጋራዋለው" የሚሉት የፖለቲካ ተንታኙ አቶ ጥላሁን፤ በተቃራኒው የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን ንግግርን ተችተውታል፡፡

ተንታኙ "ኢትዮጵያ በሁሉም አቅጣጫ ከጎረቤት ሀገራት ጋር ውጥረት ውስጥ በገባችበት ሁኔታ፤ 'ሰላም ነን ምንም ችግር የለብንም' ብለው መናገራቸው ተገቢ አይደለም" ሲሉ ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡

በተመሳሳይ በብልፅግና ፖርቲ አምስተኛ ዓመት ምስረታ ማጠቃለያ ፕሮግራም ላይ የተገኙት የኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ "ኢትዮጵያ ያለፉትን አምስት ዓመታት ከጎረቤት ሀገራት ጋር በትብብር እየሰራች ነው" ያሉ ሲሆን፤ "ኢትዮጵያን ሊያፈርስ የሚችል አንዳች ሀይል የለም" ሲሉም አክለዋል።

ይህንን በሚመለከት ሀሳባቸውን ያጋሩን እናት ፓርቲ የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ ዶክተር አሰፋ አዳነ በበኩላቸው፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በቀጠናው ጉዳይ ላይ የሰጡን ሀሳብ "ተገቢ ያልሆነ ሀሳብ" ሲሉ ገልጸውታል፡፡

በተለይም 'ከማንኛውም የውጭ አካል ጋር ምንም ዓይነት ችግር የለብንም' መባሉን የገለጹት የፓርቲው የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ፤ "መሬት ላይ ያለውን እውነታ ይሄንን አያሳይም" ብለዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስተሩ ይህንን ይበሉ እንጂ ኢትዮጵያ በግልፅ ባይገለፅም ከኤርትራ ጋር እንዲሁም ከሶማሊያ ጋር ይፋዊ እሰጣ ገባ ዉስጥ መግባቷ ግልጽ መሆኑን የፖለቲካ ፓርቲዎች እና ተንታኞች ለአሐዱ ገልጸዋል፡፡