መጋቢት 11/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የሕዝብ ተወካዮች ምር ቤት በዛሬው ዕለት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት የመንግሥትን የግማሽ ዓመት አፈፃፀም ሪፖርት አድምጧል፡፡

የምክርቤቱ አባላት የመንግሥትን የግማሽ ዓመት ሪፖርት መነሻ በማድረግ፤ ለጠቅላይ ሚኒስተር ዐቢይ አሕመድ ጥያቄዎችን አቅርበዋል፡፡

ከቀረቡት ጥያቄዎች መካከልም የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) እና የሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት አባሉ ዶክተር ደሳለኝ ጫኔ ያነሱት ይገኝበታል፡፡

ዶ/ር ደሳለኝ "ባለፉት 7 ዓመታት በተለይም በኦሮሚያ፣ በአማራ እና በሌሎችም ክልሎች የሚፈፀሙ የጦር ወንጀሎችን ለፍርድ ማቅርብ ለምን አልተቻለም? የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የመሰሉ ጉዳዮች ውጤታማ እንዲሆኑ ከተፈለገ በተለይም በኦሮሚያ እና አማራ ክልል የተኩስ አቁም መደረግ አለበት" ብለዋል፡፡

Post image


አክለውም "ታጣቂዎቹ ወደ ሰላም የሚመጡበት መንገድ በሙሉ አሟጠው እንዲሰሩ" ሲሉም በወከላቸው "የባህርዳር ሕዝብ እና በኢትዮጵያ ህዝብ ሥም እጠይቃለው" ብለዋል፡፡

ከእርሳቸው በተጨማሪ በርካታ ምክር ቤቱ አባላትም "በኢትዮጵያ የተሟላ ሰላም ለማምጣት ምን እየተሰራ ይገኛል? በተለይም ከታጠቁ ኃይሎች ጋር ለመወያየት የመንግሥት ቁርጠኝነት ምን ይመስላል? የቀድሞ ታጣቂዎችንም መልሶ ከሟቋቋም አንፃር የሚሰሩ ሥራዎች ምን ይመስላሉ? እንዲሁም በሰላም እንዲሁም በሰላም እጦት ምክንያት በሕዝብ የሚደርሱ እንግልትን ለመፍታት ምን እየተሰራ ነው? የሚሉ ጥያቄዎችን ለጠቅላይ ሚኒስትሩ አቅርበዋል፡፡

Post image


የኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድም ከምክር ቤት አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች በሰጡት ማብራሪያና ምላሽ "መንግሥት መሬትን ሲወስድብህ ተወው፣ ይወሰደው፤ ወይም በሕዝብ የተመረጠን መንግሥት ማውረድ እፈልጋለሁ ሲል መንግሥት ዝም ብሎ መመለከት የለበትም" ብለዋል፡፡

"መንግሥት ሰላም ያስቀደመ መሆን ይገባዋል፡፡ ሰላም ያደፈረሰ ነገር ሲኖርም ወደ ገፊያ ከመግባት በፊት መመልከት የሚኖርበት ነገር ያሳፈልጋል" ሲሉም ተናረዋል፡፡

"ኢትዮጵያ ውስጥ ሁለት ችግር አለ" ያሉት ጠቅላይ ሚንስትሩ፤ ዋናው የመጀመሪያው የመጠፋፋት ባህል ነው፤ ሁለተኛው ደግሞ የወታደራዊ መንግሥት እሳቤ ነው" ሲሉ ገልጸውታል፡፡

"በድርድር እና በውይይት የሚባል ልምምድ ባለመኖሩ ምክንያት አብዛኛው ፖለቲከኛ በመገዳደል የማመን አባዜ ዛሬም ችግር ሆኖብናል" ብለዋል፡፡

"የፍረጃ ችግር ኢትዮጵያ ውስጥ በስፋት አለ" ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ "ካዛንቺስ የመሰለ የሱ መንደር እንደዚህ አምሮበት ሲታይ የሚያደንቅ አንድ ፓርቲ የለም" ሲሉ ተናግረዋል፡፡

"በአንድ እግራቸው በርሃ በአንድ እግራቸው ፓርላማ ያሉ አካላት አራት ኪሎ የመግባት አባዜያቸው የሚለቃቸው አይደሰለም" ሲሉም ለምክር ቤቱ አባላት በሰጡት ምላሽ እና ማብራሪያ ገልጸዋል፡፡

#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ