መጋቢት 11/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ስብሰባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት እየተካሄደ ይገኛል፡፡

የምክር ቤቱ አባላት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ከነሷቸው ጥያቄዎች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፡-
👉 የባህር በር ለማግኘት እየተሄዱ ያሉ የዲፕሎማሲያ አካሄዶች ያስገኙት ውጤት ምንድን ነው? የባህር በር ጥያቄ ሕጋዊ እና ፍትሃዊ በሆነ መንገድ እልባት እንዲያገኝ የተከናወኑ ሥራዎችን፣ የተገኙ ውጤቶች እና ቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ማብራሪያ ቢሰጥ?
👉 የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል የሰላም እፎያታ ቢያስገኝም፤ በስምምነቱ መሰረት ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ የሚያስችሉ የስምምነት ነጥቦቹ በምን ደረጃ ላይ ይገኛሉ? የሰላም ስምምነት አፈጻጸሙስ በምን ደረጃ ላይ ይገኛል?
👉 በትግራይ ክልል እየታየ ያለው ወቅታዊ ሁኔታ ወደግጭት እንዳያመራና ዳግም ጦርነት እንዳይቀሰቀስ ምን እየተሰራ ይገኛል?
👉 በተለያዩ አካባቢዎች የሚስተዋለው መገዳደል፣ መጠፋፋት እና የፖለቲካ ተቃርኖ ዛሬም ዋጋ እያስከፈለን በመሆኑ፤ መንግሥትና መሪው ፓርቲ ችግሮችን ሰላማዊ በሆነ መንገድ በመፍታት ላይ በተሰሩ ሥራዎች የተገኘ ውጤት ምን ይመስላል?
👉 በሀገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች ታጥቀው ከሚንቀሳቀሱ አካላት ጋር ልዩነቶችን በውይይት ለመፍታት ምን እየተሠራ ነው?
👉 ታጣቂዎችን የመልሶ ማደረጃት ሥራ በምን ደረጃ ላይ ይገኛል?
👉 በሰላም እጦት ምክያት በበርካታ የሀገሪቱ አካባቢዎች በሕዝብ ላይ የሚደርሰውን እንግልት ከመሰረቱ ለመፍታት ምን እየተሠራ ነው?
👉 የፍትሕ ተደራሽነት እና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ከመሰረቱ ለመፍታት መንግሥት በቀጣይ ምን ለመስራት አስቧል?
👉 ሴክተር መሥሪያ ቤቶች ከአሥር ዓመቱ ስትራቴጅክ እቅዱ አንፃር ያላቸው አፈፃጸም ምን ይመስላል?
👉 በስድስት ወር ውስጥ የመንግሥት ወጪና ገቢ ምን እንደሚመስል ማብራሪያ ይሰጥበት?
👉 በተለያዩ ዘርፎች የሚስተዋሉ ብልሹ አሰራሮችን በዘላቂት ለመፍታት በቀጣይ የሚቀመጡ አቅጣጫዎች ላይ ማብራሪያ ቢሰጥ?
👉 በአምራች ዘርፉ ያለውን የጥሬ ዕቃ እና የሌሎች የአቅርቦት ችግሮ ለመፍታት መንግሥት ምን እየሠራ ይገኛል?
👉 የ10 ዓመቱን ስትራቴጂክ ዕቅድ ማሳካት መቻላችንን የሚያመላክቱ መስፈሪያዎች ምንድን ናቸው? ፤ ሴክተሮችስ ከዚህ ዕቅድ ጋር ምን ያህል ተናበው እየሰሩ ነው?
👉 መንግሥት በድጎማ የሚያቀርበው ነዳጅ በሕገ-ወጥ መንገድ እንዳይሸጥ ምን አይነት ጠንካራ እርምጃዎች እየተወሰዱ ነው?
👉 በአሁኑ ሰዓት የመንግሥት ሠራተኛን ጨምሮ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ዜጎች በኑሮ ውድነት እየተቸገሩ ባሉበት ሁኔታ እንዴት የዋጋ ግሽበት ቀንሷል ሊባል ይችላል? የሚሉት ይገኙበታል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከምክር ቤቱ አባላት ለሚነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ እንደሚሰጡ ይጠበቃል፡፡
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ