ባለስልጣኑ ኢትዮጵያ በአዘርባጃን በተካሄደው የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ላይ ተፈፃሚ ለማድረግ ቃል ከገባችባቸው ጉዳዮች መካከል አንዱ የፕላስቲክ ብክለት መከላከል መሆኑን ጠቅሶ፤ የአዲስ አበባ ከተማ ተግባራዊ እንዲያደርግ መጠየቁን አስታውቋል።

ለዚህም ኢንዱስትሪዎች ከሚያመነጩት በተጨማሪም በህብረተሰቡ ያለውን የፕላስቲክ አጠቃቀም መስተካከል ካልተቻለ፤ ከተማዋ ካላት የሕዝብ ብዛት አንፃር ጉዳቱ አደገኛ የሚባል መሆኑን የባለስልጣኑ ከፍተኛ ተመራማሪ አቶ ሙላቱ ወሰን ለአሐዱ ተናግረዋል።

Post image

በአዲስ አበባ ያሉ አምራች ኢንዱስትሪዎች ለአካባቢ ብክለት የሚወስዱት ሚና ከፍተኛ መሆኑን የገለጹት ተመራማሪው፤ ተደጋጋሚ ማሳሰቢያ ሲሰጣቸው መቆየቱን አንስተዋል።

የከተማ መስተዳድሩ የአለም የጤና ድርጅትን ጨምሮ ሌሎች ረጂ ተቋማት ጋር በተደረሰው ስምምነት መሰረትም፤ ማስተካከል እንደሚያስፈልግ መወሰኑን ነው የገለጹት።

ከዚህ በመነሳትም የአየር ንብረት ተርቋሪዎች የተሰጠውን ምክረ ሐሳብ በመጥቀስ፤ የቅድሚያ ቅድሚያ መሰራት ያለባቸው ጉዳዮች መሆናቸውን አፅንኦት ሰጥተውበታል።

ኢትዮጵያ ኮፕ 29 ጨምሮ የተለያዩ አለም ዓቀፍ የአየር ንብረት ለውጥ የተመለከቱ ጉባኤዎች ላይ ስትሳተፍ መቆየቷን ይታወቃል።

ባለፈው ጊዜም በተሳተፈችበት ጉባኤ የፕላስቲክ ብክለት ለማስወገድ ቃል ከተገቡ ጉዳዮች መካከል እንደሚገኙበት ከባለስልጣኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።