ጥር 13/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ኦቪድ ሪል ስቴት በዛሬው ዕለት በጥይት ቤት ቅርጫፉ ያስመረቀውን ሦስት ብሎኮች ያስመረቀ ሲሆን፤ አዲስ የሚጀምረውን ግንባታም በይፋ አስተዋውቋል፡፡
የድርጅቱ የፕሮጀክት ኃላፊ ኖላዊ ተፈራ በዛሬው ዕለት ከምርቃቱ በተጓዳኝ የሽያጭ ሥራም መጀመሩን የገለጹ ሲሆን፤ በዚህ መሰረት በዚህ ሁለት ዓመር ውስጥ ግንባታዎች በአጠቃላይ እንደሚጨረሱ አመላክተዋል፡፡
ኦቪድ ሆልዲንግ ግሩፕ ከ40 በላይ ከሚሆኑ የድርጅቱ እህት ኩባንያዎች ጋር በጋራ በመሆን ቴክኖሎጂን በመጠቀም ዋጋን የመቀነስ ሥራ እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡
ጊዜን ማሳጠር የሚችሉ ቴክኖሎጂና አቅርቦ ሰንሰሎትችን በተሻለ መጠን በጥሩ መንገድ በመጠቀም በምዕራፍ ሁለት የተጀመረው ሥራ በሁለት ዓመት ውስጥ ተጠናቆ ለተጠቃሚ እንደሚያስርከብ ገልጸዋል፡፡
አቶ ኖላዊ በአሁን ሰዓት የሚገነቡት ሕንፃዎችን ማንኛውንም አካል የመግዛት አቅም ያማከለ እና ጥንካሬውን የጠበቀ ግንባታ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ከዚህ በፊት በአዋሪ ከመንግሥት ጋር በመሆን ወደ 70 ሕንፃዎችን በመገንባት ለመልሶ ማልማት ለተነሱ ዜጎች እንዳስረከቡም ጨምረው ተናግረዋል፡፡
ከዚህ ባለፈም ከሥራ ዕድል ፈጠራ አንፃር ጥይት ቤት ሳይትን ጨምሮ ከአንድ ሺሕ በላይ ዜጎች የሥራ ዕድል እንደተፈጠረላቸውም ገልጸዋል፡፡
አሁን ላይ የተገነቡት እና የሚገነቡት ቤቶች በምን ያህል ዋጋ እየቀረቡ ስለመሆናቸው ግን ኃላፊው ከመናገር የተቆጠቡ ሲሆን፤ "በቀጣይ ይገለጻል" ብለዋል፡፡
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ