ጥር 8/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በካናዳ የሥራ እና ትምህርት ዕድል ለማመቻቸት ሕጋዊ ውክልና በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞትዮስ (ዶ/ር) የተሰጣቸው በማስመሰል ሕገ ወጥ ደብዳቤ አዘጋጅተው እያሰራጩ ያሉ አካላት መኖራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

Post image

የሚኒስትሩ ሥም ተጠቅሶ በተለያዩ የማህበራዊ ሚድያ አውታሮች እየተዘዋወረ የሚገኘው ደብዳቤ ሀሰተኛ መሆኑንም ገልጿል።

እንዲህ አይነቱን የወንጀል ተግባር እየፈፀሙ የሚገኙ አካላትን በሕግ ተጠያቂ ለማድረግ ከሚመለከታቸው ጋር እየተሰራ መሆኑን ሚኒስቴሩ አመላክቷል።

ሕብረተሰቡም ይህንን ተገንዝቦ ራሱን ከአጭበርባሪዎች እንዲጠብቅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሳስቧል።

#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ