ጥር 8/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚሰሯቸው የጥናት እና የምርመር ሥራዎች ለመጠቀም በአንድ ላይ አለማደራጀታቸው ችግር እየፈጠረ መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።
በትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ የልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ኮራ ጡሽኔ በርካታ የምርምር ሥራዎች እና ተመራማሪዎች ቢኖሩም፤ 'ምን ችግር ፈትተዋል?' የሚለውን እና ውጤቱ ላይ ማተኮር እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።
ነገር ግን የሚደረጉ የምርምር ሥራዎች በአንድ ላይ ማሰባሰብ አለመቻሉን ገልጸዋል።
ስለሆነም ጥናቶችን በማሰባሰብ እና 'የሚሰሯቸው ሥራዎች ምን ያህል ውጤታማ ሆነዋል?' የሚለውን መመዘን እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።
በቅርቡ በትምህርት ሚኒስቴር እና በከፍኛ የትምህርት ተቋማት የተደረገው ስምምነት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ ምን ያህል ብቁ ተማሪዎችን አፈሩ? ምን አይነት ችግር ፈቺ ጥናት እና የምርምር ሥራዎችን ሰሩ የሚለውን ለመፈተሸ የሚያስችል ነው ተብሏል።
በአንጻ የሚደረጉ ጥናት እና ምርምሮችን ወስዶ የሚጠቀም አካል አለመኖሩን ጥናት እና ምርምር አድራጊዎች ሲናገሩም ይደመጣል።
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ