መጋቢት 10/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ላይ ምርጫ ሲያስፈጽሙ የነበሩ ግለሰቦች ከ2013ዓ.ም ጀምሮ የእውቅና ሰርትፍኬት እንዲሰጣቸው በተደጋጋሚ ጥያቄ ቢያቀርቡም መልስ እንዳላገኙ ለአሐዱ ገልጸዋል፡፡

በ2013 ዓ ም ምርጫ ዘመን በተለያዩ ቦታዎች ላይ መስፈርቱን የሚያሟሉ ሰዎችን ምርጫ ቦርድ በመመልመል እንድያስፈጽሙ ማድረጉን የገለጹት ቅሬታ አቅራቢዎች፤ አብዛኛዎቹ የእውቅና ሰርትፍኬት የተሰራላቸው ሲሆን ያልደረሳቸው እንዳለም ተናግረዋል፡፡

ሀገራዊ ምርጫውን ሲከናወን ለሁለት ቀን ማለትም ለ48 ሰዓት ያህል ያለ እርፍት ምርጫውን ሲያስፈጽሙ እንደነበር የገለጹም ሲሆን፤ል ይህንን ጉዳይ በተመለከተ ምርጫ ቦርድን ሰርተፍኬቱን እንዲሰጣቸው ሲጠይቁ 'በኦን ላይን ይሰጣችኋል' ጠብቁ መባላቸውን አንስተው "በአሁኑ ሰዓት ደግሞ ምንም አይነት የሰርትፍኬት ሥራ እንደሌለ ተነግሮናል" ብለዋል፡፡

ይሁን እንጂ "ለተወሰኑት ተሰቷቸው ለሌላው የሚከለከልበት አግባብ ሊኖር አይገባም" ያሉት ቅሬታ አቅራቢዎች፤ ለደከሙበት እና ለለፉበት ማስረጃ እንዲሰጣቸው በተደጋጋሚ ቢጠይቁም ምንም መልስ እየተሰጣቸው ገልጸዋል፡፡

አሐዱም ይህንን ጉዳይ በተመለከተ የኢትዮጲያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድን ጠይቋል፡፡

ከቦርዱ ባገኘነው መረጃ መሠረትም እስካሁን እንደዚህ አይነት ቅሬታ እንዳልመጣለት እና ለሁሉም የምርጫ አስፈጻሚዎች ሰርትፍኬ እንዲደርስ በሚያስችል መልኩ የኦን ላይን ስርአት ተዘርግቶ ሲሰራ እንደነበር የተገለጸ ሲሆን፤ አልደረሰንም የሚለው ቅሬታ ትክክል እንዳሆነ ለማወቅ ተችሏል፡፡

ይሁን እንጂ ችግር ካለም ተቋሙ ድርስ በመምጣት መፍታት እንደሚቻልና የሚነሱ ቅሬታዎችን በተመለከተ በውይይት መፍታት እንደሚገባ ቦርዱ አጽንኦት ሰጥቷል፡፡

#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ