በክፍለ ከተማው ወረዳ 07 ሚካኤል ቤተክርስቲያን ጀርባ በአንድ መጋዘን በሕገወጥ መልኩ በርበሬን ከባዕድ ነገር ጋር በመቀላቀል ምርት ሲመረት በቁጥጥር ሥር መዋሉን ነው፤ የክፍለ ከተማው የሕገ ወጥ ንግድ ቁጥጥር ግብረ ሃይል ያስታወቀው።
የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ የንግድ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አሸናፊ ፍቅሬ፤ በኅብረተሰቡ ጤናን ደህንነት በሚጎዳ መልኩ በርበሬን ከባዕድ ነገር ጋር በመቀላቀል ለገበያ ለማዋል ሲመረት በቁጥጥር ሥሩ መዋሉን የገለጹ ሲሆን፤ ወደ ገበያ ቢገባ በኅብረተሰቡ ላይ ከፍተኛ የጤና ጉዳትም ሊያስከትል እንደሚችል ተናግረዋል።
አክለውም ጽ/ቤታቸው በእንደዚህ አይነት ሕገወጥ ተግባር ላይ ተከታታይነት ያለው እርምጃ እየወሰደ እንደሚገኝና በሕገወጦች ላይ የሚወሰዱ አስተዳደራዊና ሕጋዊ እርምጃዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል፡፡
ኅብረተሰቡም እንደዚህ አይነት ሕገወጥ ተግባራት ሲመለከት፤ ለሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪ አቅርበዋል።