"እድሜቸው ከ30 እስከ 40 የሆኑት በኤች አይቪ ቫይረስ የተያዙ እና በወሲብ ንግድ ላይ የተሰማሩ ሴቶች የበለጠ ተጋላጭ ናቸው" ያሉት አቶ ወንደሰን፤ ጥንቃቄ ካልተደረገ ከ 18 ዓመት በታች ያሉትንም እንደሚያጠቃ አንስተዋል፡፡

አክለውም "የማህፀን በር ካንሰር ምንም አይነት ምልክት ሳያሳይ ከ10 እስከ 20 ዓመት ይቆያል" ሲሉ ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት በ1 ሺሕ 453 የጤና ተቋማት የማህፀን በር ጫፍ ካንሰር ቅድመ ልየታ እየተሰጠ እንደሚገኝም ተናግረዋል።

የማህፀን በር ጫፍ ካንሰር በሽታ "ሂውማን ፓፒሎማ ቫይረስ" በሚባል ረቂቅ ተዋህስ የሚከሰት በሽታ መሆኑንም አመላክተዋል፡፡

በአለም አቀፍ ደረጃ በበሽታው የሚያዙ ሰዎች 5 መቶ 30 ሺሕ ሲሆኑ፤ ከ2 መቶ 70 ሺሕ በላይ የሚሆኑ ሴቶች እንደሚሞቱ ተገልጿል፡፡

በሽታው በሴቶች ላይ ከሚከሰቱ የካንሰር ዓይነቶች ከጡት ካንስር ቀጥሎ በሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ በሽታ መሆኑም ተነግሯል።