መጋቢት 16/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በአዲስ አበባ ከተማ አራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ሰባራ ባቡር አካባቢ የተፈጠረውን የእሳት አደጋ መቆጣጠር መቻሉን ክፍለ ከተማው አስታውቋል፡፡

ባልታወቀ ምክንያት የተከሰተው እሳት አደጋ በእሳት አደጋ ሰራተኞች፣ ነዋሪዎች እና በፀጥታ አካላት የተነሳውን እሳት መቆጣጠር መቻሉ ነው የተነገረው።

Post image

የእሳት አደጋ መንስኤውን በቀጣይ እንደሚያሳውቅ የገለጸው ክፍለ ከተማው፤ በአደጋው ከንብረት ውጭ በሰው ሕይወት ላይ የደረሰ አደጋም ጉዳት አለመኖሩን አመላክቷል፡፡

#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ