ጥር 22/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በቦሌ ቡልቡላ ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 በተለምዶ 93 ማዞሪያ የሚባለው አካባቢ የእሳት አደጋ መከሰቱን አሐዱ በቦታው ሆኖ መመልከት ችሏል።
በአሁኑ ሰዓት አደጋውን ለመቆጣጠር ጥረት እየተደረገ ሲሆን፤ አራት የእሳት አደጋ ተሽከርካሪዎች እንዲሁም አንድ የውሃ ቦቴ በቦታው መድረሳቸውን አሐዱ በስፍራው በተገኘበት ሰዓት ተመልክቷል።
የእሳት አደጋው በአካባቢው በሚገኝ ጅምር ሕንጻ ላይ ነው የተነሳው።
እሳቱን ለማጥፋት የአደጋ ሠራተኞች በስፍራው ላይ ርብርብ እያደረጉ ሲሆን፤ የጸጥታ ሃይሎች በቦታው ተገኝተው ሰዎችን ከአካባቢው ዞር እንዲሉ በማድረግ ላይ ናቸው።
በአደጋው የተጎዳ ሰው ወይም ንብረት ስለመኖሩ እስካሁን የተባለ ነገር የለም። በአካባቢው የነበሩ የአይን እማኞች እንደገለጹት እሳቱ የተነሳው ወደ 11:10 አካባቢ ነው።
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ