ጥር 22/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የተባበሩት ዐረብ ኢምሬቶች ባዘጋጀችው የዓለም አቀፍ የ2025 ፈጣን ምላሽ አሰጣጥ ውድድር (SWAT Challenge) ላይ ለመወዳደር ወደ ዱባይ ያቀናው የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ስዋት ቡድን ልምምድ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡
በዚህ የዓለም አቀፍ የ2025 ፈጣን ምላሽ አሰጣጥ ውድድር ላይ ለመወዳደር ወደ ዱባይ ያቀናው የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ስዋት ቡድን በአልሩዋይ ከተማ በሚገኘው የስዋት ቻሌንጅ ማሰልጠኛ ማሰልጠኛ ማዕከል ልምምድ እያደረገ መሆኑ ነው የተገለጸው።
የስዋት ቡድኑ፤ በታክቲካል ኦፕሬሽን ቻሌንጅ፣ በጥቃት ቻሌንጅ፣ በVIP አመራር የማዳን ተልዕኮ፣ በከፍተኛ ታወር መውጣትና መውረድ እንዲሁም በመሰናክል ኮርስ ዘርፎች እንደሚወዳደር ተገልጿል።
ውድድሩ እ.ኤ.አ የካቲት 1-5 እንደሚካሄድም ታውቋል።
በውድድሩም አሜሪካና ቻይናን ጨምሮ ከ50 ሀገራት የተውጣጡ ከ120 በላይ የSWAT ቡድኖች እንደሚሳተፉ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ መረጃ አመላክቷል።
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ