ጥር 28/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሐረርጌ ዞን ሜታ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ8 ሰዎች ሕይወት ማለፉን የዞኑ ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል፡፡

አደጋው ከጅቡቲ ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ የነበረ የጭነት ተሽከርካሪ ከቆቦ ከተማ ወደ ድሬዳዋ ሲያመራ ከነበረ ዶልፊን ጋር በመጋጨቱ መከሰቱን መምሪያው ገልጿል፡፡

Post image

በተፈጠረው አደጋም የ8 ሰዎች ሕይወት ማለፉ የተነገረ ሲሆን፤ በተጨማሪም በሦስት ሰዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱን የፖሊስ መምሪያው የኮሙኒኬሽን ኃላፊ ረዳት ኢንስፔክተር ካስዬ አበበ መናገራቸውን ኤፍ ኤም ሲ ዘግቧል፡፡

#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ