ታሕሳስ 29/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ዛሬ ከምሽቱ 12: 00 ሰዓት ጀምሮ የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ፤ ጭማሪ መደረጉን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ታሕሳስ 20 ቀን 2014 ዓ ም ባደረገው መደበኛ ስብሰባ ባስተላለፈው የነዳጅ ውጤቶች የዋጋ ግንባታ የአፈጻጸም ውሳኔ መሰረት ከታሕሳስ 29 ቀን 2017 ዓ.ም ከምሽቱ 12 ፤00 ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ ተግባራዊ የሚሆነው የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ እንደሚከተለው እንዲሸጥ በመንግሥት መወሰኑ ተገልጿል።
በዚህም መሰረት ፦
👉 አንድ ሊትር ቤንዚን 101.47 ብር
👉 አንድ ሊትር ናፍጣ 98.98 ብር
👉 አንድ ሊትር ኬሮሲን 98.98 ብር
👉 የአውሮፕላን ነዳጅ 109.56 ብር
👉 አንድ ሊትር ከባድ ጥቁር ናፍጣ 105.97 ብር
👉 አንድ ሊትር ቀላል ጥቁር ናፍጣ 108.30 ብር ሆኖ እንዲሸጥ መወሰኑ ተገልጿል።
በአዲሱ የዋጋ ክለሳ መሠረት ቤንዚን አንድ ሊትር ቀድሞ ሲሸጥበት ከነበረው 91.14 ብር ዋጋ የ10 ብር ከ33 ሳንቲም ጭማሪ የተደረገበት ሲሆን፤ በተመሳሳይ ቀድሞ በሊትር 90.28 ብር ሲሸጥ የነበረው ነጭ ናፍጣ የ8 ብር ከ70 ሳንቲም ጭማሪ ተደርጎበት መሸጥ ጀምሯል።
በነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ጭማሪ ተደረገ
የቤንዚን ዋጋ ላይ የ10 ብር ከ33 ሳንቲም ጭማሪ ተደርጎበታል